icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ስለ ኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 ፣ ዞምቢ ሞድ ሊያውቋቸው የሚገቡ አዳዲስ ጉዳዮች 

ኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 ከዚህ በፊት የነበሩ ምዕራፎቹን ሊያስንቅ የሚችል የዞምቢዎች ሞድን በማካተት አዲሱን ምዕራፍ ይዞ በመምጣት ላይ ይገኛል። በቅርቡ በተደረገው የኤክስ-ቦክስ ጌሞች ኤግዚቢሽን እና የብላክ ኦፕስ 6 ዝግጅት ፣ ህዳር 25 እንደሚለቀቅም ተገልጿል። 

ይህ የፍራንቻይዙ አንድ አካል የሆነው ፣ የዞምቢዎች ሞድ በብላክ ኦፕስ 6 ከአስደናቂ ማሻሻያዎች ጋር የሚመለስ ሲሆን ፥  ተጫዋቾች በተዘጋጁ ልዩ አካባቢዎች ላይ ፣ ለሰዓታት ከዞምቢዎች ጋር ከባድ እና አስደቂ የሆኑ ውጊያዎችን ማድረግ ያስችላቸዋል። 

የብላክ ኦፕስ 6 ፣ የዞምቢዎች ሞድ ቁልፍ ማሻሻያዎች 

አዲስ ካርታዎች፡ ተርሚነስ እና ላይቤሪቲ ፎልስ 

  • ተርሚነስ፡- በተርሚነስ ፊሊፒንስ ባህር ውስጥ በሚገኝ ሚስጥራዊ ቦታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ፣ ይህ ቦታ በድብቅ ሚስጥሮች እና ውስብስብ እንቆቅልሾች የተሞላ ጨለማ አካባቢም ነው።  

  • ላይቤሪቲ ፎልስ፡- ይህ ቦታ ቦዞምቢዎች የተወረረ አሜሪካ ውስጥ የሚገኝ ገጠራማ መንደር ሲሆን ፣ ይህ በውስብሰብ እንቆቅልሾች ፣ እና ድበቅ ምስጢራት የተሞላ ቦታ ነው። 

እነዚህ ካርታዎች የተለያዩ አዳዲስ ባህሪያትን እና ማሻሻያዎችን ይዘው የሚመጡ ሲሆን ፣ ከነዛም መካከል የተሻሻለ የእንቅስቃሴ ነፃነት ፣ የምስል ጥራት ፣ የድምጽ እና የጦር መሳሪያዎችን ያካትታል። እነዚህ ተጨማሪ ማሻሻያዎችም ከመቼውም ጊዜ የበለጠ መሳጭ እና አስደሳች ተሞክሮን የመስጠት አቅማቸው ከፍተኛ ነው። 

ታዋቂውን የፐርክ-ኤ-ኮላስ ማሽኖችን በማካተት ፣ ከዚህ በፊት የነበሩት የዞምቢዎች ሞድ ሽልማቶችም የሚመለሱ ሲሆን ፣ ተጫዋቾቹ እንደ ባለብዙ ተጫዋቾች ሞድ ከእያንዳንዱ ተልዕኮ በፊት ፣ አንደኛ ደረጃ መሳሪያዎች ፣ ሁለተኛ ደረጃ ጦር መሳሪያዎች ፣ የቅርብ ርቀት መሳሪያዎች ፣ እንዲሁም የተለያዩ ከባድ ፣ ታክቲካዊ እና ተቀያሪ መሳሪያዎቻቸውን ፣ ዝግጁ ሊያደርጉ ይገባል። 

የዞምቢዎች ሞድ እስከ 4 ተጫዋቾችን ማሳተፍ የሚችል ሲሆን ፣ አጠቃላይ የአጨዋወት ጥራቱ ካለፉት ክፍሎች የላቀ እንደሚሆን አያጠራጥርም። ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት ፣ ትሬያርች ስለ ኮል ኦፍ ዲውቲ የሚያዘጋጃቸው ፅሁፎች ላይ መመልከት ይችላሉ። 

ኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 ፣ ጥቅምት 25 በይፋ እና ፣ ነሐሴ 30 ደግሞ ለቅድመ-ጨዋታ ይለቀቃል። ከዞምቢዎች ጋር ለሚደረገው አስደናቂ ጦርነት ይዘጋጁ። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !