
ሆነር ኦፍ ኪንግስ ለመጀመሪያ ጊዜ በቻይና እ.ኤ.አ. 2015 የተለቀቀ ተወዳጅ እና በመቶ ሚልዮኖች ተጫዋቾችን ማፍራት የቻለ የሞባይል MOBA (ኦንላይን ባለብዙ ተጫዋቾች ጌም ሲሆን ፥ ቻይና ውስጥ ትልቅ ተቀባይነትን በማግኘት ፣ አሁን ደግሞ ወደ ሞዕራቡ ዓለም አድማሱን በማስፋት ላይ ይገኛል።
እ.ኤ.አ. ሰኔ 20 ፣ 2024 ለአውሮፓ ተጫዋቾች ፣ አይፎን እና አንድሮይድ ላይ በይፋ ለጨዋታ የበቃ ሲሆን ፣ ይህ ጌም ተጫዋቾች ፣ ባለ ልዩ ችሎታ ተቀናቃኞችን መቆጣጠር እና የጠላትን መሠረት ማፍረስ የሚያስችላቸውን ልዩ ተሞክሮ ያቀርባል።
ጨዋታው በቻይና ኢ-ስፖርት ውስጥ በጣም ተወዳጅ የሆነ እና ፣ ኃያላን የሚባሉ ትላልቅ ቡድኖች በኪንግ ፕሮ ሊጉ (KPL) ውስጥ የሚያወዳደር ጌም ነው። የኢ-ስፖርት የዓለም ዋንጫ አካል የነበረም ሲሆን ፣ ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ምን ያህል ተቀባይነትን እያገኘ መሆኑን ትልቅ ማሳያ ነው። አዘጋጆቹ አውሮፓም ውስጥ ተመሳሳይ ተቀባይነት እንደሚኖረው እና ጠንካራ ተወዳዳሪ ማህበረሰብ እንደሚፈጥር እምነታቸውን ገልፀዋል።
የሆነር ኦፍ ኪንግስ ተጫዋቾች ፣ ሰኔ 20 በይፋ ከመጀመሩ በፊት በመመዝገብ ፣ ልዩ ሽልማቶችን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ፥ ከሽልማቶቹም መካከል፡-
ዪንግ የተባለ ገፀ-ባህሪን ፣ እስከ ልዩ ማስጌጫዎቹ በነፃ!
ለደረጃ 1፡ 500 አልማዞች
ለደረጃ 2፡ 2000 አርኬን ፍራግመንቶች
ለደረጃ 3፡ 5000 የኮከብ ድንጋዮች
ለደረጃ 4፡ ማንኛውንም ገፀ-ባህሪዎች መሞከር የሚያስችሉ ፣ 20 ትኬቶች
ሆነር ኦፍ ኪንግስ ፣ ሰኔ 20 ፣ 2024 የአውሮፓ ገበያን ለመቆጣጠር ተዘጋጅቷል። ጌሙ በርካታ ገፀ-ባህሪዎችን እና ማራኪ የሆነ ጨዋታን ወደ አውሮፓ እያመጣ ሲሆን ፣ ጦርነቱን ከጅምሩ በመቀላቀል ፣ ይህን አስደሳች እና በቻይና ትልቅ ተቀባይነት ያገኘ ጌም ላይ ቀድመው በመመዝገብ ቀድመው ያጣጥሙ!