
ፎርትናይት መስከረም 17 በጀመረው ምዕራፍ 5 ፣ ክፍል 4 Day of Dooms የሚባል አዲስ የጌም ሞድን አስተዋውቋል። የጀግኖች ጦርነትን መሰረት አድርጎ የተሰራው ይህ ሞድ የተጫዋጮችን ትኩረት እያሳበ ይገኛል።
Day of Doomsን ለማግኘት ወደ ፎርትናይት ዋና ገጽ በመሄድ ከሌሎች የጌም ሞዶች ጋር ተዘርዝሮ ያገኙታል።
ይህ ሞድ 32 ተጫዋቾችን በሁለት ቡድኖች በመክፈል ዱም ሄንችማን ከአቬንጀሮች ጋር እንዲፋለሙ የሚያስችል የጌም ሞድ ነው።
ዱም ሄንችማን፦ ግባቸው አቬንጀርሶቹ ድጋሚ ህይወት እንዳይዘሩ ለማድረግ ፣ 6 Arcane Artifacts መሰብሰብ ሲሆን ፣ ሁሉም አቬንጀርሮች ከተወገዱ በኋላ አሸናፊ ይሆናል።
አቬንጀርሶች፦ ግባቸው የዱም ኃይሎችን ማሸነፍ እና አርቲፋክቶችን እንዳይሰበስቡ ማስቆም ሲሆን ፥ ዱም ሄንችማኖች በተደጋጋሚ ህይወት መዝራት ስለሚችሉ ፣ ህይወት የመዝራት ኃይላቸውን በመቀማት ማሸነፍ ነው።
ያስታውሱ! ይህ ለተወሰኑ ጊዜያት የተዘጋጀ ሞድ በመሆኑ ከመጥፋቱ በፊት ይሞክሩት!