
በቫልቭ የተሰራው ፣ የባለ ብዙ ተጫዋቾች እና የሶስተኛ ወገን ዕይታን የሚጠቀመው ዴድሎክ ፥ ገና በሙከራ ደረጃ ላይ ቢሆንም ትልቅ ተወዳጅነትን ማግኘት ችሏል። በእስቲም ግብዣ በኩል አሁን ላይ ወደ 200,000 የሚጠጉ ዕድለኛ ተጫዋቾች ቤታውን በመጫወት ላይ ይገኛሉ።
MMR በውድድር ጨዋታዎች ውስጥ የብቃት ደረጃዎን የሚገልጽ ድብቅ ቁጥር ሲሆን ፣ በአጨዋወት ብቃት ላይ በመመስረት ፣ ቡድኖችን ለማመጣጠን ፥ በጌሙ የግጥሚያ ሲስተም ጥቅም ላይ የሚውል ፣ ፍትሃዊ ግጥሚያዎችን ማስፈፀሚያ መንገድ ነው።
ቫልቭ የMMR መረጃ ማግኛ መንገዶችን በቅርቡ እንዲቋረጡ ያደረገ ቢሆንም ፣ ከመስከረም 2 2024 በፊት ያደረጓቸውን ጨዋታዎች ግን እነዚህን ሂደቶች በመከተል ፡ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።
1. የዴድሎክ ትራከር ድረ-ገጽን ይክፈቱ
የተጫዋቾችን የጨዋታ ስታቲስቲክስ መረጃ የያዘውን የየዴድሎክ ትራከር ድረ-ገጽን ይክፈቱ።
2. የስቲም አካውንትዎን በመጠቀም ይግቡ
በዋና ገጹ ከላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ ያለውን "Login" ን የሚለውን ይጫኑ እና በስቲም አካውንትዎ ይግቡ። ይህም ድረ-ገጹ የዴድሎክ የጨዋታ ስታቲስቲክስዎን እንዲያገኝ ያስችለዋል።
3. ስታቲክስዎን ይመልከቱ
አንዴ ከገቡ በኋላ ፣ ሁለት አስፈላጊ ክፍሎችን ያገኛሉ፡-
መለያ፡- እዚህ ውስጥ መረጃው ከመገደቡ በፊት በነበረዎ አጨዋወት ላይ በመመስረት ከMMR ጋር የሚመሳሰል የDLT ቁጥርዎን ያገኛሉ።
የመሪዎች ሰንጠረዝ፡- እዚህ ሰንጠረዝ ላይ ፣ ምን ያህል ጊዜ እንደሞቱ ፣ የደረሰብዎት ጉዳት ፣ እና KDA (ግድያ ፣ ሞት ፣ እገዛ) ያሉ ዝርዝር ስታቲስቲክስዎን ማየት ይችላሉ።
4. ደረጃዎን ያነፃፅሩ
የእርስዎን ስታቲስቲክስ ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር በማነጻጸር ፣ የብቃት ደረጃዎን ማወቅ ይችላሉ። የDLT ደረጃ አሰጣጥ ትክክለኛ MMR ደረጃ ባይሆንም ፣ ከሌሎች ተጫዋቾች አንፃር ግን ያለዎትን ተቀራራቢ ግምት ማወቅ ያችሎታል።
ማስታወሻ፡- ከመስከረም 2፣ 2024 በኋላ ለተደረጉ ግጥሚያዎች የአፈጻጸም መረጃን የመከታተያ አማራጭ ዘዴዎችን ለማቅረብ ዴድሎክ ትራከር አዲስ አሰራሮችን እየዘረጋ ስለሚገኝ ፣ ይህን አዲስ ዝማኔ ለማግኘት ድረ-ገፁን መከታተልዎን አይርሱ!