icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ፎርትናይት በኢፒክ ጌምስ መደበር አማካኝነት ወደ ሞባይል ስልኮች ተመልሷል! 

ፎርትናይት በኢፒክ ጌምስ አማካኝነት ወደ iOS እና አንድሮይድ ሞባይል ስልኮች በድጋሚ ተመልሷል። ጌሙ የሞባይል ስልኮች ላይ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ የባትል ሮያል አድናቂዎች ከዓመታት በኋላ እንደገና በስልካቸው መጫወት ይችላሉ። 

ፎርትናይትን ሞባይል ስልኮች ላይ እንዴት መጫን ይቻላል? 

  1. የኢፒክ ጌምስ መደብር መተግበሪያን ፣ ከስልክዎ የመተግበሪያዎች መደብር ያውርዱ። 

  1. መተግበሪያውን በመክፈት ፣ የጌሞች ዝርዝሮችን ይክፈቱ። 

  1. ከዝርዝሮቹ መካከል ፎርትናይትን ይምረጡ (በተጨማሪም ፎል ጋይስ እና ሮኬት ሊግ ሳይድስዋይፕን ማግኘት ይችላሉ)። 

  1. በመጨረሻም ማውረጃውን ይጫኑ። 

የማይታወቁ መተግበሪያዎች ፈቃድ (unknown app permissions) የሚል ማሳወቂያ ካጋጠመዎ፡- 

  1. የስህተት ማሳወቂያወን ይጫኑ። 

  1. "Allow from this source." የሚለውን ይጫኑ። 

  1. የመጫን ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ Playን በመጫን ፣ ጨዋታዎን መጀመር ይችላሉ። 

ለሞባይል ተጫዋቾች የተዘጋጀ ልዩ ሽልማቶች 

የኢፒክ ጌምስ መደብርን በመጠቀም ፎርትናይትን ወደ ሞባይል ስልኮቻቸው ለሚያወርዱ ተጫዋቾች ልዩ ሽልማቶችን እየሰጠ ሲሆን ፣ ከሽልማቶቹም መካከል የካታሊና ገፀ-ባህሪ አንዱ ነው። 

እንደ Xbox እና Ubisoft ያሉ ሌሎች ድርጅቶች በክላውድ ጌሚንግ አማካኝነት የሞባይል ጌሞች አገልግሎት እየሰጡ በመሆናቸው ፣ ኢፒክ ጌምስ ይህን አማራጭ ይዞ መመለሱ ትልቅ ስኬት ነው።  

አሁን ተጫዋቾች ፎርትናይት እና እንደ ፎል ጋይስ እና ሮኬት ሊግ ሳይድስዋይፕን እና ሊሎች ታዋቂ ጌሞችን የሞባይል ስልኮቻቸውን በመጠቀም መጫወት ይችላሉ! 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !