icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የGTA-6 መውጫ ቀን ወደ 2026 ተዘዋውሯል? ሮክስታር በስተመጨረ ምላሽ ሰጥቷል!  

ባለፉት ሳምንታት ስለ GTA 6 መውጫ ቀን ፣ በተለይ ደግሞ የመለቀቂያው ቀን ወደ 2026 ተዘዋውሯል የሚሉ እና የመሳሰሉ ጭምጭምታዎች ዓለም ላይ በሚገኙ ተጫዋቾች ዘንድ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኖ ነበር። በስተመጨረሻም ፣ ሮክስታር ጌምስ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቷል። 

GTA-6 እ.ኤ.አ 2025 እንደሚለቀቅ ተረጋግጧል! 

በሮክስታር ይፋዊ መግለጫ መሰረት GTA 6 መውጫ ቀን ወደ 2026 ተቀይሯል የሚለው ወሬ የሀሰት መረጃ መሆኑን በመግለጽ ፣ ቀድሞ ባስቀመጠው ዕቅድ መሰረት በ2025 ጌሙን እንደሚለቅ አረጋግጧል። ትክክለኛ የመልቀቂያውን ቀን ባይገልፁም ፣ ነገሮች በታቀደው መሠረት እየሄዱ መሆናቸውን ለአድናቂዎቹ አስረግጠው ተናግረዋል። 

የGTA-6 መውጫ ቀን ወደ 2026 ተዘዋውሯል የሚለው የሀሰት ወሬ ሲናፈስ የነበረበት ምክንያት ፣ ሮክስታር ከዚህ በፊት የሰራቸውን አንጋፋ ጌሞች መውጫ ቀን በማዘግየቱ ምክንያት በአንዳንድ ተጫዋቾች ዘንድ ይህ ድጋሚ ሊሆን ይችላል የሚል ምክንያት ይዘው ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ሆኖም ግን ስቱዲዮው GTA 6 ኔክስት-ጂን ኮንሶሎች ማለትም በፕለይስቴሽን 5 እና በኤክስ-ቦክስ X/S ላይ እንደሚለቀቅ ተናግረዋል። በፒሲም የሚጠበቅ ቢሆንም ፣ ሮክስታር ስለዚህ ጉዳይ እስካሁን ምንም ያለው ነገር የለም ፣ ከዚህ ቀደም በለቀቋቸው እንደ GTA V እና Red Dead Redemption 2 ካሉ ጌሞች በመነሳት ፣ GTA-6 ከአንድ ዓመት በኋላ ፒሲ ላይ ሊለቀ እንደሚችል መገመት ይቻላል። 

በአጠቃላይ ሮክስታር GTA 6 እስከ 2026 እንደማይዘገይ በማረጋገጥ ውጥረቱን ለማርገብ እየሞከረ ቢሆንም ፣ ነገር ግን በተጫዋቾች ዘንድ ያለው ጉጉት እንደቀጠለ ይገኛል። GTA 6 እጅግ አስገራሚ እና ትልቅ ተወዳጅነት እንደሚኖረው ከወዲሁ መገመት የሚቻል ጉዳይ ነው። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !