icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 ቤታ ላይ የሚገኙ የAMES-85 ምርጥ አባሪ መሳሪያዎች  

ኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 በዚህ ዓመት በጉጉት ከሚጠበቁ ጌሞች መካከል አንዱ ነው። ይህንንም አስመልክቶ ፣ አክቲቪዥን ሁለት ቤታዎችን አዘጋጅቷል ፥ አንደኛው ከነሐሴ 30 እስከ መስከረም 4 የተደረገ ዝግ የቤታ ፕሮግራም ሲሆን ፣ ሁለተኛው ደግሞ ከመስከረም 6 እስከ 9 የየተደረገው ክፍት ቤታ ፕሮግራም ነበር። ተጫዋቾች በእነዚህ ፕሮግራሞች ላይ AMES-85 የተባለውን የመካከለኛ ርቀት የጦር መሳሪያን እና ሌሎች የተለያዩ መሳሪያዎችን የመሞከር እድል አግኝተው ነበር። ይህን የጦር መሳሪያ እንዴት በአግባቡ እና ከፍተኛ አቅሙን እንዴት አድርገው መጠቀም እንደሚችሉ ፣ ቀጥለን መመሪያ አዘጋጅተናል። 

ኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 ቤታ ላይ የሚገኙ የAMES-85 ምርጥ አባሪ መሳሪያዎች  

AMES-85 በሰከንዶች ብዙ ቀልሃዎችን መተኮስ የሚያስችል እና በመካከለኛ ርቀት ውጊያዎች ላይ ጠላቶችን በፍጥነት ለማስወገድ የሚያስችል ተመራጭ መሣሪያ ነው። 

AMES-85 ጋር አብረው እንዲጠቀሟቸው የሚመከሩ አባሪዎች፡ 

  • አፈሙዝ፦ እርግጫ መቆጣጠሪያ 

  • እጀታ፡- ቋሚ መያዥያ 

  • ካርታ፡- ባለብዙ ቀልሃ ካርታ 

  • ኦፕቲክ፡- ሜርሊን ሚኒ 

  • የአተኳኮስ ዓይነት፦ የተኩስ እርግጫን መቋቋም የሚችል ስፕሪንግ 

መሳሪያዎች፡ 

  • አባሪ መሳሪያ፡- ታንቶ SMG 

  • የቅርብ እርቀት መሳሪያ (ሜሌ)፡- ጩቤ 

  • ታክቲካል፡- ስቲም ሾት 

  • ከባድ መሳሪያ፡- ሴምቴክስ (ፈንጂ) 

  • ተጨማሪ ማሻሻያ፡- የጥቃት ጥቅሎች 

ሽልማቶች፡ 

  • ሽልማት 1፡- ፍላክ ጃኬት 

  • ሽልማት 2፡- ዲስፓቸር 

  • ሽልማት 3፡- ጊርሄድ 

  • ልዩ የውጊያ ብቃት፦ ስትራቴጂስት 

  • ዋይልድ-ካርድ፦ ኦቨር ኪል 

እነዚህ አባሪዎችን መጠቀም በመካከለኛ ርቀት ውጊያዎች ላይ እንደልብዎ እየተንቀሳቀሱ ፣ ያልተዛነፈ የተኩስ ዒላማዎችን ማድረግ ያስችልዎታል ፥ እንዲሁም ግዴታ እነዚህን እንደወረደ መጠቀም የማይጠበቅብዎ እና እንደ እጨዋወትዎ እና የግል ፍላጎቶችዎ አስተካክለው መጠቀም የሚችሉ ቢሆንም ፣ ከላይ ያስቀመጥናቸውን አባሪዎች መጠቀም ግን ይበልጥ ውጤታማ ያደርግዎታል።  

ሙሉ ጨዋታው ጥቅምት እ.ኤ.አ በ25 ፣ 2024 ላይ ፒሲ ፣ ፒኤስ4 እና 5 ፣ ኤክስ-ቦክስ1 እና X/S ላይ ጨዋታ ማለፊያን ጨምሮ ለጨዋታ ይበቃል። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !