
በቅርቡ ፎርትናይት ባወጣው ዝማኔ ፣ የአይረን ማን የበረራ እና የውጊያ ትጥቆች ተጫዋቾች የቶኒ ስታርክን አቅም ሙሉ በሙሉ በመጠቀም ጠላትን መቆጣጠር አስችሏቸዋል። እነዚህን ትጥቆችን እንዴት ማግኘት እና በውጊያ ወቅት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ቀጥለን እናያለን።
የአይረን ማን ትጥቆችን የት ማግኘት ይቻላል?
የአይረን ማን ትጥቆችን የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ማግኘት የሚቻል ሲሆን፡-
የግሪም ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍል (ድልድዩ አካባቢ)
የናይትሮድሮም ሰሜናዊ ክፍል
የኦሊምፐስ ተራራ ምዕራባዊ ክፍል
የሬክለስ ሬልዌይስ ደቡባዊ ክፍል (በረሃው ላይ)
የዱም ኮርትያርድ ደቡባዊ ክፍል (የባቡር ሀዲዱ አካባቢ)
ትጥቆቹን ማግኛ ዘዴዎች
የአይረን ማን ሳጥኖች፡- እያንዳንዱ የማረፊያ ነጥቦች ፣ የበረራ ወይም የውጊያ ትጥቆችን በውስጣቸው ሊይዙ ይችላሉ።
የአይረን ማን አርማ፡- ከሦስተኛው ክብ ማዕበል በኋላ ፣ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የአይረን ማን አርማ የሚታዩ ሲሆን ፣ ይህም አጋጣሚ ትጥቆቹ ወደሚገኙበት ተንቀሳቃሽ የትጥቅ ማከማቻ ይመራዎታል።
የበረራ ትጥቆች
አገልግሎት፡- በከፍተኛ ፍጥነት እና ከፍታ ላይ መብረር የሚያስችል ሲሆን ፣ ይህም በውጊያ ወቅት ቦታዎችን እንደልብ ለመቀያየር እና ጠላቶችን ለማምለጥ ያስችላል።
ጥቅም፡- እንደልብ መንቀሳቀስ የሚያስችል ሲሆን ፣ ምንም ሳይገድብዎ ቦታዎችን ማሰስ እንዲችሉ እና ጠላቶችን ከላይ ሆነው እንዲያጠቁ ያስችልዎታል።
ጉዳት፡- የውጊያ ትጥቅ ከሌለዎት ፣ በበረራ ወቅት የጦር መሳሪያዎችን መጠቀም አይችሉም።
የውጊያ ትጥቆች
ይህ የውጊያ ትጥቅ ሁለት ከባድ መሳሪያዎችን የሚያካተት ሲሆን፦
ሪፐልሰርስ፡- 30 ነጥብ የሰውነት ክፍሎች ላይ እና 45 ነጥብ ደግሞ ከአንገት በላይ ጉዳት የማድረስ አቅም ያለው ሲሆን ፣ ከመጠን በላይ እንዳይግልብዎ መጠንቀቅዎን አይዘንጉ።
ዩኒቢም፦ በቀጥታ ጥቃት ወቅት 90 ነጥብ ጉዳት ማድረስ የሚችል ሲሆን ፥ ይህም መዋቅሮችን ለማማውደም እና ጠላቶችን በፍጥነት ለማስወገድ እጂግ ተመራጭ ነው።