
አይረን ማን ፎርትናይት ላይ መካተተን ተከትሎ ፣ ታዋቂው የስታርክ ኢንደስትሪ ጠመንጃ ለተጫዋቾ ቀርቧል። ይህ ጠመንጃ ሳምንታዊ ተልዕኮዎችን በድል ለመወጣት እና ውጊያዎችን ለማሸነፍ የሚያስችል ከባድ እና ኃይለኛ መሳሪያ ሲሆን ፣ ይህን ጠመንጃ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ እና መጠቀም እንደሚችሉ ቀጥለን እናያለን፦
የሚከተሉትን ሂደቶች በመከተል የስታርክ ኢንደስትሪ ጠመንጃን ማግኘት ይችላሉ፦
በቅድሚያ ለረጅም ርቀት ውጊያ የሚሆን ጠመንጃ ወይም ሽጉጥ እንዳለዎት ካረጋገጡ በኋላ ፣ በካርታው ላይ የሚገኘው ቢጫ ነጥብ ላይ ይረፉ።
እዚህ አካባቢ ላይ የሚገኙ ቁልፍ ቦታዎች ላይ የሚያንዣብቡ የስታርክ ኢንዱስትሪ ድሮኖችን ይፈልጉ።
ድሮኖቹን እንዳገኙ ተኩሰው በመጣል ፣ ሬር እና ሌጀንደሪ የሆኑ የኢነርጂ ጠመንጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።
እድለኛ ሆነው ፣ ሌጀንደሪ የሆነ ጠመንጃው ካገኙ ፣ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ እና ፈጣን የማቀባል አቅም ያለው ጠመንጃ እጅዎ ውስጥ አስገቡ ማለት ነው።
ለረጅም ርቀት ውጊያዎች፡- ይህ የኢነርጂ ጠመንጃ ያልተዛነፈ የማነጣጠር አቅም እና ከፍተኛ ጉዳትን ማድረስ የሚችል ከባድ መሳሪያ ነው።
ዒላማ (ADS)፡- የማነጣጠር አቅሙ የልብ አድርስ መሆኑ ፣ ለረጅም ርቀት ውጊያ ከፍተኛ ውጤትን ያስገኛል።
የቅደመ-ጨዋታ ጥቅም፡- የአይረን ማንን ከባድ መሳሪያ ቀጣይ ተልዕኮዎች ላይ ከማግኘትዎ በፊት ፣ ይህን ጠመንጃ የጌሙ ጅማሮ ላይ እጅዎ ላይ ማስገባት እጅግ ውጠታማ ያደርግዎታል።
እነዚህ ጠመንጃዎች ተወዳጅ ስለሆኑ በእነዚህ አካባቢዎች ከሚገኙ ሌሎች ተጫዋቾች ታላቅ ፉክክርን ስለሚኖር እና ግብዓቶችዎን ከመነጠቅ ለማዳን ይዘጋጁ!