
አዲሱ EA FC 25 ላይ አስደናቂ ግቦችን ማግባት ብቻ ሳይሆን ፣ ደስታዎን በልዩ ልዩ ጭፈራዎች መግለጽ የሚችሉባቸው መንገዶች አሉ ፥ ከነዛም መካከል በጣም ተወዳጅ የሆነው "የሀመር ዳንስ" በተጨዋቾች ዘንድ ተወዳጅነትን እያገኛ መጥቷል።
ባሳለፍነው ክረምት ታም ሲር ፣ ከፓያ ቡድን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው "Coup du Marteau" የተሰኘው ሙዚቃ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እና የተጨዋቾች ክለቦች ላይ ተልቅ ተቀባይነትን አግኝቷል። ማራኪ የሙዚቃ ምቱ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግጥሙ የተነሳ በሺዎች ዘንድ ተወዳጅነት ከማትረፉ በተጨማሪ የራሱ የሆነ ልዩ ዳንስ እንዲፈጠርለት ምክንያት ሆኗል። EA FC 25 ላይ ከመካተቱ ብዙም ሳይቆይ ፣ ተጫዋቾች ጎል ካስቆጠሩ በኋላ ድላቸውን የሚያበስሩበት ተመራጭ ሙዚቃ መሆን ችሏል።
ይህን ጭፈራ ጎል ካስቆጠሩ በኋላ ለመጠቀም ፣ እነዚህን ሂደቶች ይከተሉ፡-
R1 ተጭነው ይያዙ
የግራ አቅጣጫን ይጫኑ
ወዲያው የቀኝ አቅጣጫን ፣ ሁለት ጊዜ በፍጥነት ይጫኑ
እነዚህን ሂደቶች ተከትለው እንደጨረሱ ፣ ገፀ-ባህሪዎ የሀመር ዳንሰን መጨፈር ይጀምራል።
ገፀ-ባህሪዎ ውጤት ካስመዘገበ በኋላ ፣ በታም ሰር እና በፓያ ቡደን የተሰራውን "Coup du Marteau" የተሰኘውን መዚቃ በመጠቀም ልዩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የሚችሉ ሲሆን፥ ይህ ዳንስ ጨዋታዎ ይበልጥ አስደሳች ለማድረግ እና ጎሎች ሲያቆጥሩ ተቃራኒ ቡድነን ለማበሳጨት ሊጠቀሙት የሚችሉበት አዝናኝ መንገድ ነው። ቀጣይ ግጥሚያዎ ላይ ይሞክሩት ፣ ይወዱታል!