icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ትሮን እና ላይቤሪቲ ላይ የታንክ ገፀ-ባህሪን እንዴት መጫወት እና እንዴት የጦር-መሳሪያዎችን መጠቀም ይቻላል? 

ትሮን እና ላይቤሪቲ ላይ የታንክ ገፀ-ባህሪዎችን በአግባቡ ለመጠቀም ፥ ጥንካሬ ፣ ቁጥጥር እና የጠላት ትኩረትን የመሳብ ችሎታዎች ወሳኝነት አላቸው። ይህን ሚናንም ስኬታማ ሆነው ለመወጣት የሚያስችሎዎትን ፣ ምርጥ የጦር መሳሪያዎችን ዝርዝር አዘጋጅተናል። 

ለታንክ ገፀ-ባህሪዎች የሚሆኑ የጦር መሳሪያዎች 

ኃያሉ ሠይፍ፦ ለብቻቸው ለሚጫወቱ ተጫዋቾች ተመራጭ ሲሆን ፣ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሱ የህይወት ነጥቦችዎን ከፍ ማድረግ የሚያስችልዎ መሳሪያ ነው። ምንም እንኳን ከጠላት ብዙ ጥቃት ሊደርስብዎ ቢችልም ፣ የህይወት ነጥብ ቋትዎ እና ከፍተኛ የማጥቃት አቅምዎ ከሚደርስብዎ ጉዳት ጋር የሚነፃፀር አይደለም። 

ሠይፍ እና ጋሻ፡- ይህ መሳሪያ ለቡድን ጨዋታዎች ተስማሚ የሆነ ጥምር መሳሪያ ሲሆን ፣ የሚሰነዘርብዎትን ጥቃቶች እየተከላከሉ የጠላትን ትኩረት መሳብ ያስችልዎታል። መከላከያ ጋሻው ከፍተኛ አቅም ያለው በመሆኑ ፣ ከጠላት የሚመጡ የጥቃት ማዕበሎችን መቋቋም እና ቡድንዎን በሚገባ መጠበቅ ያስችልዎታል።. 

ቁልፍ ብቃቶች 

  • ጥንካሬ:- ለማንኛውም የታንክ ገፀ-ባህሪ ቁልፍ የሆነ ማሻሻያ ሲሆን ፣ የህይወት ነጥቦችዎን እና የመከላከል አቅምዎን በመጨመር ፣ የበለጠ ጠንካራ እንዲሆኑ ያስችልዎታል። 

  • ቅልጥፍና፡- የጥቃት ፍጥነትዎን እና አጠቃላይ የማጥቃት ችሎታዎችዎን ያሳድጋል። 

  • ጥበብ፦ ሠይፍ እና ጋሻ እየተጠቀሙ ከሆነ ፣ ጠላቶች ላይ የተተገበሩ ማንኛውም የአቅም ማዳከሚያ ድግምቶች ቆይታን እንዲራዘም ያደርጋል። 

ይህ ማሻሻያ ከፍተኛ ጉዳት በሚደርስብዎ ወቅት የህይወት ነጥብ ቋትዎን ለማስተካከል ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ፥ ጠላቶችን ቶሎ ለማስወገድ እንደ Death Blow ወይም Guillotine Blade ያሉ ክህሎቶችን ይጠቀሙ። በዛ ያሉ የጠላት ቡድኖች ላይ ጥቃት ለመጣል ከፈለጉ ደግሞ ፣ እንደ አጥፊ አውሎ-ንፋስ ያሉ ክህሎቶችን ቅድሚያ በመስጠት ይጠቀሙ። 

ቁልፍ ችሎታዎች፡- ዴዝ ብሎው ፣ ጊውሎቲን ብሌድ ፣ አውዳሚ አውሎ ነፋስ። 

መሳሪያዎች፡- የጥቃት ነጥብዎን ከፍ ለማድረግ ፣ ከባድ ጥቃቶችን ማድረስ የሚያስችሉ መሳሪያ ይምረጡ። 

የእዚህ ማሻሻያ ዋና ዓላማ የጠላትን ትኩረት በሚሰቡበት ወቅት ፣ ሊደርሱ የሚችሉ ከባድ ጥቃቶችን መከላከል ሲሆን ፥ የመከላከል አቋምዎን ሳይለቁ  የመልሶ ማጥቃት ክህሎቶችን መጠቀምዎን አይርሱ። ይህም ጥቃቶችን በሚከላከሉበት ወቅት የቡድን አባሎችዎ DPS ላይ እንዲያተኩሩ ያስችላቸዋል። 

ቁልፍ ችሎታዎች፡ ታውንት ፣ መመከቻ ጋሻ ፣ መልሶ ማጥቃት 

መሳሪያዎች፡- የሚደርሱ ከባድ ጥቃቶችን መከላከል እንዲያስችልዎ፣ የጋሻዎን ጥቃት የመከላከል አቅም ማሻሻል ላይ ያተኩሩ። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !