icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

EA Sports FC 25 ላይ የፍፁም ቅጣት ምት ዓይነቶች እና ዘዴዎች 

በ EA Sports FC 25 ጥሩ የፍፁም ቅጣት ምቶችን ከመምታትዎ በፊት ፣ ለፍፁም ቅጣት ምት የሚሆን ጥሩ ክህሎት ያለው ተጫዋች በመምረጥ ይጀምሩ። ለቅጣት ምት የሚሆን ክህሎት ያላቸው ተጫዋቾች የምንላቸው፦ 

  • ዒላማዎችን መምታት የሚችል እና ጥሩ የማለም ክህሎት ያለው። 

  • ለፈጣን እና ቅፅበታዊ ምቶች ፣  ከፍተኛ ኃይል ያላቸው ምቶችን መምታት የሚችል።  

  • ጫናን መቆጣጠር እና ተረጋግቶ መምታት የሚችል ተጫዋችን ያካትታል። 

ለፍፁም ቅጣት ምት የሚሆን ጥሩ ክህሎት አለው ብለው ያመኑትን ተጫዋች ከመረጡ በኋላ ፥ ኳሱን ወደ ፈልጉበት አቅጣጫ ለመምታት በቀኝ በኩል የሚገኘውን ማሽከርከሪያ በመጠቀም በቀስታ ያንቀሳቅሱ። የላይኛው ወይም የታችኛውን ማዕዘኖች በግብ ጠባቂዎች ለመያዝ አስቸጋሪ በመሆናቸው እነሱን ቢጠቀሙ ይመከራል። 

ኃይል አሰጣጥ፡- መምቻዎቹን (O/B)ን ቀስ ብለው በመጫን ይምቱ። ያስውሱ! መምቻውን በኃይል ከተጫኑት ኳሱ ግቡን ስቶ ወደ ላይ ሊወጣብዎት ይችላል። ዒላማዎን ያልሳተ ምት ለመምታት በኳሱ ዙሪያ ያለው ክብ እየጠበበ ሲሄድ ይምቱ። 

ልዩ ወይም የቅንጦት ምቶችን (Panenka)፦ መምታት ከፈለጉ ፣ L1/LB በመያዝ እና መምቻውን በስሱ በመጫን በመሬት ወደ ግቡ መሃል መምታት ወይም ሎጨ ግብ ማግባት ይችላሉ። 

ቁልፍ ነጥቦች፡- 

  • ፍፁም ቅጣት ምቱን ከመምታትዎ በፊት ፥ በተረጋጋ እና በሰከነ መንፈስ ዒላማዎን ያስተካክሉ። 

  • አንድ ዓይነት ዒላማዎችን በመምታት ቀጣዩ ምትዎ በቀላሉ የሚገመት እንዳይሆን ፣ ያልተጠበቁ ዒላማዎችን እና የምት ዓይነቶችን በመቀላቀል ይጠቀሙ። 

  • የፍፁም ቅጣት ምት ብቃትዎን ለማሻሻል ፣ የልምምድ ሞድ ላይ ከተለያዩ ተጫዋቾች ጋር በመሆን ይለማመዱ። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !