
በመጨረሻም ከሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ፣ ሀንተር x ሀንተር ምዕራፍ 401 ጥቅምት 6 ፣ 2024 ሳምንታዊው ሾነን ጃምፕ ዝርዝር ላይ ተመልሷል። የእዚህ ተከታታይ አዘጋጅ የሆነው ዮሺሂሮ ቶጋሺ በጤና ጉዳዮች ምክንያት ቋሚ የመልቀቂያ መርሐ-ግብሮችን መከተላ ባለመቻሉ ፣ ወደፊት የሚለቀቁ አዳዲስ ምዕራፎች ላይ ክፍተቶች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ተነግሯል።
ሀንተር x ሀንተር ምዕራፍ 402 እሁድ ፣ ጥቅምት 13 2024 ፣ አመሻሽ በ11፡00 ሰዓት ላይ ማንጋፕላስ ላይ የሚለቀቅ ሲሆን ፣ ዋን ፒስ ላይ እንደሆነም ፣ ከመልቀቂያው ቀን አስቀድሞ ጥቅምት 10 ላይ አንዳንድ ፍንጮች ሊኖሩ እንደሚችሉም ተነግሯል።
አዘጋጁ ቶጋሺም እስከ ምዕራፍ 419 ድረስ አዘጋጅቶ እንደጨረሰም ተናግሯል። ይህም የሀንተር x ሀንተር አድናቂዎች በቋሚነት ይዘቶችን ማግኘት እንዲችሉ ዋስትና የሚሰጥ ቢሆንም ፣ የጤናው ጉዳይ አዳዲስ ምዕራፍ መልቀቂያ ቀናት ላይ ክፍተት ሊፈጥር እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልጋል።
የዚህ `ሙንላይት`የተባለው አዲስ ምዕራፍ አዲስ ገፀ-ባህሪ ሎንግሂ ክህሎቶችን በመዋስ ወይም ድርጊቶችን በመገደብ ኮንትራቶችን መመስረት የሚያስችለውን የነን ቴክኒኩ የሆነው "Transparent Words"ን ያሳያል። ኩራፒካም የኔቴሮ ልጅ መሆኗን እና ከተወለደችበት ጊዜ አንስቶም የኔን ችሎታዎች እንዳላትም ገልጻለች። በተጨማሪም ሎንግሂ የተረገመ እንደሆነ እና ፣ እርግማኑም ሲሞት ስራውን የሚጀምር ይሆናል።
ለእዚህ አዲስ ከሆኑ ፥ ሀንተር x ሀንተር በዮሺሂሮ ቶጋሺ የተፈጠረ ማንጋ ሲሆን ፣ አባቱን ለማግኘት ሲል አዳኝ መሆን ስለ ሚፈልገው የጎን ፍሪክስን ታሪክ ያትታል። ታሪኩ በአስደናቂ ፍጥረታት የተሞላ እና በጃፓን ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ማንጋዎችን ማነሳሳት የቻለ "ኔን" ስለተባለ ዓለም ውስጥ ስለሚገኙ ጀብዱዎች ፣ ስልቶች እና ምስጢሮችን የሚዳሰስ ታሪክ ነው።