icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ትሮን እና ላይቤሪቲ ላይ ለጀማሪዎች የሚሆኑ የጦር-መሳሪያዎች 

ትሮን እና ላይቤሪቲ ላይ ተልዕኮዎችን የሚመጥኑ የጦር-መሳሪያዎችን ቀድመው መምረጥ እና ማዘጋጀት በቡድንዎ ውስጥ የሚኖርዎትን ሚና በአግባቡ ለመወጣት እና ተልዕኮዎችን በድል ለመወጣት የሚያስችልዎ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው። ከዚህ ቀጥሎ ተልዕኮዎን በድል ለመወጣት ይረዳዎ ዘንድ ፣ ለጀማሪ የሚሆኑ የጦር መሳሪያዎችን እና እጠቃቀማቸውን ቀጥለን አዘጋጅተናል፡- 

ጩቤ 

ይህ ጩቤ ፈጣን ውጊያ እና ቅልጥፍናን ለሚሹ ተጫዋቾች የሚሆን መሳሪያ ሲሆን ፥ ጠላት ላይ ከባድ ጥቃትን ያለምንም ፋታ ለማድረስ የሚያስችል የቅርብ ርቀት መሳሪያ ነው። ጥቃት መመከቻ እና መሰንዘሪያዎችን አንድ ላይ በማጣመር የጠላት ጥቃትን እየመከቱ ፣ ጥቃት ማድረስ ያስችልዎታል። 

የፈውስ በትር 

የቡድን አጋሮችዎን ደህንነት ለመጠበቅ እና በህይወት እንዲቆዩ ለመርዳትን ከፈለጉ የፈውስ በትርን ምርጫዎ ሊያደርጉ ይገባል። የፈውስ በትር ፈውስን እና ድጋፍን የመስጠት አቅምን የሚሰጥዎት ሲሆን ፣ ይህን መሳሪያ በመጠቀም የቡድንዎን ህልውና መጠበቅ መቻል ብቻ ሳይሆን የውጊያ አፈፃፀማቸውን ማሳደግ ያስችልዎታል። 

ኃያሉ ሠይፍ  

የጦር ጓዶችዎን የጦር አውድማዎች ላይ በፊት-አውራሪነት የሚመሩ ከሆነ እና የቡድን አጋሮችዎን ከጠላት ከሚሰነዘሩ ጥቃቶች መከላከል የሚፈልጉ ከሆነ ይህ መሳሪያ ለእርስዎ ነው። ይህ ግዙፍ መሳሪያ ከጠላት የሚመጡ ከባድ ጥቃቶችን እየተቋቋሙ በተመሳሳይ ሰዓት ፣ ጠላት ላይ ከባድ ጫና ማሳደር የሚያስችልዎ መሳሪያ ነው። ይህንን መሳሪያ በአግባቡ መጠቀም ከቻሉ ፣ በጣም አስቸጋሪ እና ከባድ በሆኑ ውጊያዎች ወቅት ፣ ቡድንዎ መቶ በመቶ የሚተማመንብዎት ፊት አውራሪ ያደርግዎታል። 

ትሮን እና ላይቤሪቲን በድል ለመጀመር ፣ ከአጨዋወት ዘይቤዮ እና ፍላጎትዎ ጋር የሚስማማ መሳሪያ ቀድሞ በመምረጥ ውጤታማ መሆን ይችላሉ። መልካም ጨዋታ! 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !