icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

EA Sport FC 25 ውስጥ ስለሚገኘው FUT ሻምፒዮና ሞድ ማወቅ ያለብዎ ጉዳዮች 

በ EA FC 25 ውስጥ የሚገኘው የFUT ሻምፒዮን ሞድ ፣ ያለምንም ጥርጣሬ ለአልቲሜት ቡድን ተጫዋቾች እጅግ ፈታኝ ከሆኑ ሞዶች ውስጥ አንዱ ነው። ይህ ሞድ በየሳምንቱ መጨረሻ ተጫዋቾችን የሚያወዳደር ሲሆን ፣ የአሸናፊዎች ሰንጠረዥ ላይ ለመስፈር እና ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ለማግኘት የኖከአውት ውድድሮች ላይ መሳተፍ ይኖርብዎታል። 

FUT ሻምፒዮና ላይ እኝዴት መሳተፍ ይቻላል? 

የFUT ሻምፒዮንስ ውድድር ከአርብ እስከ ሰኞ የሚቆይ እና እስከ 20 የሚደርሱ ግጥሚያዎች ላይ መጫወት የሚያስችልዎ ውድድር ነው። ይህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ በመጀመሪያ እንደ ሪቫልስ ያሉ ሌሎች ሞዶች ላይ ነጥቦችን በማግኘት ብቁ መሆን ይጠበቅብዎታል። የብቃት ደረጃውን ካሟሉ በኋላ የሚጠበቅብዎት የFUT ውድድሮች ላይ በቻሉት መጠን ብዙ ውድድሮችን ማሸነፍ ነው። 

ሽልማቶች 

በሁሉም ግጥሚያዎች ላይ ያለዎት የድል ብዛት የሽልማት ደረጃዎን የሚወስን ሲሆን ፥ ከፍተኛ ደረጃ ሽልማቶችን ለማግኘት ብዙ ድሎች ሊኖርዎት ይገባል። ለምሳሌ፦ ደረጃ 1 ፣ 15 ድሎች ፣ ደረጃ 10 ፣ ደግሞ 2 ድሎችን ይፈልጋሉ። ሽልማቶቹ የFUT ክሬዲቶች ፣ የተጫዋቾች ጥቅል እና ልዩ TOTW (የሳምንቱ ምርጥ ቡድን) ካርዶችን ያካትታል። 

ልዩ ሽልማቶች 

ሽልማቶች እንደየደረጃው የሚለያዩ ሲሆን ፣ ከወርቅ ጥቅሎች እስከ ልዩ ጥቅሎች ያሉ ሲሆን ፣ ለከፍተኛ ደረጃ ተጫዋቾች ደግም ፣ ልዩ የሂሮ ወይም የአይከን ካርዶች አሉ። ሽልማቶቹ በየሳምንቱ ሀሙስ ከጠዋቱ 3 ሰዓት (በኢትዮጵያ ሰዓት) ጀምሮ ለተጫዋቾች እንዲደርሱ ይደረጋል ፥ ይህም ቡድንዎን ለወደፊት ፈታኝ ውድድሮች እንዲያዘጋጁ ያስችልዎታል። 

የFUT ሻምፒዮና ቡድንዎን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ፣ ችሎታዎን ለማሳየት እና ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ማግኘት የሚችሉበት ጥሩ አጋጣሚ ነው። 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !