
የዋን ፒስ 1129 ክፍል አጀማመር ውጥረት የተሞላበት አጀማመር ነበር ፥ ይህ ክፍል የሚጀምረው በግርግር እና በጭንቀት በተዋጠች ከተማ ውስጥ ሲሆን ፣ የከተማ ነዋሪዎች በመስኮታቸው ቀዳዳ በኩል ባዩት አስፈሪ የእሳት ነበልባል ሲደነግጡ እና ሲሸበሩ ያሳያል።
ባልተጠበቀ ሁኔታ ደግሞ ፣ የፀሃዩ አምላክ እንግዳ ወደሆነ ዳዮራማ ሲገባ ፣ በአንድ ወቅት ኢር ጋድ በመባል የሚታወቀውን ጥንታዊ ሥጋ በል ጥንቸል አጽም ያገኛል ፥ በመቅደሱ መርከስ የተበሳጨውም የፀሃዩ አምላክ "እንዴት መቅደሴን ታዋርዳለህ ፣ እሱ አልበቃ ብሎስ እንዴት አገልጋዮቼን ታጠቃለህ!" በማለት ኃይል እና ንዴት በተቀላቀለ ድምጽ ይጮሃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፣ ሁሌም በትርምስ ውስጥ ቀልድ ቢጤ ጣል ማድረግ የሚወደው ሉፊ ፣ የፀሐዩ አምላክ የገነባውን ሌጎ መሰል ህንፃ ትልቁ ድመት ኢስካት እንዳያጠፋው ፣ በሁሉም ሁኔታ ቀና ነገርን የማየት ችሎታውን በሚያሳይ መልኩ ይነግረዋል።
ውጊያው በፀሐዩ አምላክ የሚተዳደር ግዛት ስር በሚገኝ ቤተመቅደስ እና ግዙፍ ዳዮራማ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን ፣ ዞሮ እና ሳንጂ በፀሐዩ አምላክ ተጠምዶ የነበረውን ወጥመድ ሲያከሽፉ ፣ ኡሶፕም አረንጓዴ ኰከብ : የራስ ቅል ቦምብን" በመጠቀም መስታወቱን ሲሰባበር ይታያል። ይህን ሁሉ ጥረታቸውንም በግርምት ሲመለከት የነበረው የፀሐዩ አምላክም ፣ የመጨረሻ ዕድል ሊሰጣቸው በመፈለግ አሽከሮቹ እንዲሆኑ ይጠይቃቸዋል።
ናሚም እንዴት የፀሐዩ አምላክ ሊያውቃቸው እንደቻለ ገራ መጋባት ውስጥ እንዳለች ፣ ሉፊ ግን ለመዋጋት ዝግጁ ሆኖ ስለነበር አራተኛውን ማርሽ በማስነሳት ፣ እጁን ብቻ ይለውጣል። ወዲያው ታሪኩ ወደ ኋላ ይመለስ እና ፣ የፀሐዩ አምላክ በአንድ ወቅት ከሉፊ ጋር ይሰራ የነበረው ግዙፉ የባሕር ወንበዴ ሮድ እንደነበር ያሳያል።
ናሚም በዙስ እገዛ ሮድን በመብረቅ ክፉኛ ትመታው እና የኮንግ ጠመንጃን በመጠቀም ግድግዳውን በማፈራረስ ፣ ከግድግዳው ባሻገር የሚገኘውን አስደናቂ ነገር ስታይ ይታያል። ይህ ክፍልም ሉፊ በሚያየው ነገር ተደንቆ ፈገግ ሲል ይጠናቀቃል።