icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ዋን ፒስ 1129ኛ ክፍል : የኤልባፍ ድብቅ ምስጢር 

የዋን ፒስ 1129ኛ ክፍል ፣ የሚጀምረው በግርግር እና በጭንቀት በተዋጠች ከተማ ውስጥ ሲሆን ፣ የከተማ ነዋሪዎች በመስኮታቸው ቀዳዳ በኩል ባዩት አስፈሪ የእሳት ነበልባል ሲደነግጡ እና ሲሸበሩ ያሳያል። የፀሃዩm አምላክ እንግዳ ወደሆነ ዳዮራማ ሲገባ ፣ በአንድ ወቅት ኢር ጋድ በመባል የሚታወቀውን ጥንታዊ ሥጋ በል ጥንቸል አጽም ያገኛል ፥ በመቅደሱ መርከስ የተበሳጨውም የፀሃዩ አምላክ "እንዴት መቅደሴን ታዋርዳለህ ፣ እሱ አልበቃ ብሎስ እንዴት አገልጋዮቼን ታጠቃለህ!" በማለት ኃይል እና ንዴት በተቀላቀለ ድምጽ ይጮሃል። 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፣ ሁሌም በትርምስ ውስጥ ቀልድ ቢጤ ጣል ማድረግ የሚወደው ሉፊ ፣ የፀሐዩ አምላክ የገነባውን ሌጎ መሰል ህንፃ ትልቁ ድመት ኢስካት እንዳያጠፋው ፣ በጦርነት መኃል ቀና ነገርን የማሳየት ችሎታውን በሚያሳይ እና ፊዝ በመሰለ መልኩ ይነግረዋል። ናሚም የአከባቢውን ካርታ ካጤነች በኋላ ፣ ከላይ የሚታዩት ደመናዎች ፣ የተንጠለጠሉ የውሸት ጥጦች እንደሆኑ እና ይህንን የጥንቆላ አካባቢ ለመሻገር ወደ ፊት መሄድ እንዳለባቸው ለቡድን አጋሮቿ ትነግራቸዋለች። 

ቦታው በፀሐዩ አምላክ የሚተዳደር ግዛት ስር አንደ ሶስተኛውን የሚይዘው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲሆን ፣ የተቀረው ደግሞ ውስብሰብ የሆነ ዳዮራማ ነበር ፣ መሃሉም ላይ በጫካ እና በውሃ የተከበበው የቢግስቴይን ቤተመንግስት ይገኛል። የፀሐዩም አምላክ ቡድኖቹን በወጥመድ ወጥመድ አዘጋችቶላቸው የነበር ቢሆንም ፣ ዞሮ እና ሳንጂ ይህን ቀድመው በማወቅ ወጥመዱን ድምጥማጡን ያጠፉታል። ዑሶፕም አረንጓዴ ኮከብ ፡ የራስ ቅል ቦምብን በመጠቀም መስታወቱን ቢሰባብረውም ፣ ግድግዳው ግን አሁንም ከጀርባው እንደተገተረ ነበር። 

ይህን ሁሉ ጥረታቸውንም በግርምት ሲመለከት የነበረው የፀሐዩ አምላክ ፣ የመጨረሻ ዕድል ሊሰጣቸው በመፈለግ አሽከሮቹ እንዲሆኑ ይጠይቃቸዋል።  ናሚም እንዴት የፀሐዩ አምላክ ስለነሱ ይህን ያህል ሊያውቅ እንደቻለ ገራ መጋባት ውስጥ እንዳለች ፣ ቾፐር `ታሶ` የሚለው ቃል ምን ማለት እንደሆነ ትጠይቃታለች። ሉፊ ግን ለመዋጋት ዝግጁ ሆኖ ስለነበር አራተኛውን ማርሽ በማስነሳት ፣ እጁን ብቻ ይለውጣል። 

ወዲያው ታሪኩ ወደ ኋላ ይመለስ እና ፣ የፀሐዩ አምላክ የግዙፎቹ የባሕር ወንበዴዎች የቀድሞው መርከበኛ የነበረው ሮድ እንደነበር ይታያል። በትዝታ ወደ ኋላ ተመልሶ እዚህ ሁኔታ እንዲገባ ያደረገውን ፣ የቀድሞ ካፒቴኑ የነበረው ሀጅሩዲን የሉፊን ግራንድ ፍሊት ለመቀላቀል የወሰነበትን ቀን አስታውሶ ፊቱ በብስጭት ሲጨስ በግልጽ ይታያል። ከዛም ወዲያው ሮድ ፣ ለናሚ የተለየ ፍላጎት በማሳየት ፣ ሉፊን እና ናሚን ለመያዝ በማሰብ ፣ ራስ በሚያስት ጋዝ ሊያስተኛቸው ሞከረ። 

ናሚም በዙስ እገዛ ከመቅጽበት ፣ ትልቅ ማዕበል እና መብረቅ በመፍጠር ሮድን በመብረቅ ክፉኛ መታ ትዘርረዋለች። ሉፊም የኮንግ ጠመንጃን በመጠቀም ግድግዳውን በማፈራረስ ፣ ሙሉው የቡድን አባላት በኢስካት በመታጀብ ወደ ወጪ መውጣት ቻሉ። ይህ ክፍልም ሉፊ ፊት ለፊቱ በሚያየው ነገር ተደንቆ ፈገግ ሲል ይጠናቀቃል። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !