
ሉፊ እና ጓደኞቹ ፣ የዋን ፒስ አድናቂዎች ሊያውቁት ስለጓጉለት ታዋቂ ደሴት ወደ ኤልባፍ ጉዟቸውን ቀጥለዋል። በጉዟቸው መኃልም ኃይለኛ ውጊያዎች እና ብዙ ልብ አንጠልጣይ ጉዳዮች ያጋጠዋቸው ሲሆን ፣ የዚህ አስደናቂ እና በጀብዱዎች የተሞላ ታሪክ ድምቀቶች መካከልም ፣ የታሪኩ ጭብጥ ከሆነው ከታዋቂው መንገድ ጋር መድረሳቸው ነው። በተጨማሪም ሉፊ አዳዲስ ስልቶችን በመፍጠር ፣ ቀስ በቀስ የጊር 5 ጥበቡን ማሳደግ ችሏል።
ሆኖም ግን የዋን ፒስ አድናቂዎች አዳዲስ ክፍሎችን በጉጉት እየተጠባበቁ እና ፣ ቡድኖቹ ወደ ታዋቂው የኤልባፍ ደሴት መቃረብ ላይ ሲደርሱ ፣ ዋን ፒስ ለተወሰነ ጊዜ መቆሙ ተነግሯል። የዚህ ተከታታዩ አዘጋጅ ኢችሮ ኦዳ ለተመልካቾች የሚመጥኑ ማሻሻያዎችን ለማድረግ እና ፍላጎታቸውን ለማሟላት ለተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ በመወሰኑ ፣ በዚህ ሳምንት ይወጣ የነበረው 1130 ክፍል እንዲዘዋወር ተደርጓል።
ዋን ፒስ በይፋ ድጋሚ ከመመለሱ በፊት ክፍል 1130 እስከ ሀሙስ ፣ ጥቅምት 31 ፣ 2024 ድረስ አምልጦ ሊወጣ የሚችል ቢሆንም ፣ በይፋ ሲለቀቅ መመልከት ለሚመርጡ ተመልካቾች ፣ እሁድ ህዳር 3 ፣ 2024 በሹኢሻ ማንጋፕላስ ላይ ይለቀቃል።
ምንም እንኳን ዋን ፒስ እረፍት መውሰዱ በአድናቂዎቹ ዘንድ ቅሬታን የሚፈጥር ቢመስልም ፣ የዋን ፒስ አድናቂዎች የኢችሮ ኦዳን ውሳኔ የሚረዱ እና የሚደግፉ ታማኝ አድናቂዎች በመሆናቸው ፣ ለመጠበቅ ዝግጁ ናቸው። እያንዳንዱ መጨረሻ የአዲስ ምዕራፍ መጅመሪያ በመሆኑ ዋን ፒስ ከዓለምአቀፍ ደጋፊዎቿ የሚጠበቅበትን ደረጃ አሟልቶ መመለሱ የማሳጠራጥር ጉዳይ ነው።