
ኦኪጂ ከአኬኑ ጋር ከፍተኛ ውጊያ ካደረገ በኋላ የአድሚራል ሥልጣኑን ለመልቀቅ ተገዷል። እንደ እድል ሆኖ ፣ ሎጊያ ዴቭል የተባለውን ፍሬው በመጠቀም በውጊያው ወቅት ተጎድቶ የነበረውን አንደኛ እግሩን በበረዶ እግር ሊተካው ችሏል።
ጋርፕ ደግሞ ፣ ኮቢን ከብላክቤርድ የባህር ላይ ወንበዴዎች ለማዳን ከኦኪጂ ጋር ያደረገው ኃይለኛ ውጊያ ፣ እድሜው ፣ የአቅሙ ማሽቆልቆል እና የሚገኝበት አስጊ ሁኔታ ተደምሮ ፣ ከአኦኪጂ ጋር የነበረውን ውጊያ እጂግ ፈታኝ አድርጎበት ሊሸነፍ ችሏል። አኮጂ በበረዶ ጦር ደረቱ ላይ የወጋው ፤ ቢሆንም እንደዕድል ሆኖ የበረዶው ቅዝቃዜ የሚፈሰውን ደም አስቁሞለት ፣ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስበት ፣ ህይዎቱ ሊተርፍ ችሏል።።
አሁን ላይ ፣ የዓለም መንግስት ጋፕ እንደጠፋ እንጂ ፣ ስለሁኔታው ምንም አይነት ተጨባጭ መረጃ የለውም። ሆኖም ግን ጋርፕ ከጦርነቱ መትረፍ ቢችልም ፣ በብላክቢርድ አማፂ ቡድኖች ታግቶ ድጋሚ ህይዎቱ አደጋ ላይ ወድቃለች።
ጋርፕ ተጎሳቅሎ እና በሰንሰለት ተተብትቦ በብላክቢርድ እስር ቤት ውስጥ ታስሮ ፣ ዕጣ ፈንታው እጅግ ጨካኝ እና የባህር ላይ ወንበዴዎች መሪ በሆነው ብላክቢርድ እጅ ላይ ትገኛለች። በጭካኔው የሚታወቀው ብላክቢርድም የጋርፕ የልጅ ልጅ የሆነው እና የብላክቢርድ ቀንደኛ ጠላት የሆነውን ሉፊን ለማስገደድ ጋፕን እንደ መደራደሪያ ሊጠቀመው አስቧል።
ይህ ሁኔታ የጋርፕ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እና የሉፊ እና የባህር ሃይሎች ሊሰጡ የሚችሉት የመልስ ምት ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት እና ታሪኩ በምን ሊቋጭ እንደሚችል አለማወቅ በዋን ፒስ አድናቂዎች ዘንድ ትልቅ ጉጉትን ፈጥሯል።