
በተጨዋቾች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው ፉትቦል ማናጀር 2025 (FM25) ህዳር ይለቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም ፣ ወደ መጋቢት 2025 እንደተዘዋወረ አዘጋጆቹ አሳውቀዋል። ስቱዲዮው በትዊተር ገፃቸው እንደገለጹት ከሆነ ፣ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈለገበት ምክንያት ጌሙን ይበልጥ አስደሳች ለማድረግ ፣ የተለያዩ ማሻሻያዎችን እና ማስተካካያዎችን ለማድረግ ታስቦ እንደሆነ አሳውቀዋል።
እንደተለመደው ፉትቦል ማናጀር በየዓመቱ ፣ እንደ መጫወቻ መድረኩ ሁኔታ በርካታ እና የተለያዩ ስሪቶች ይለቀቃል ፣ እነሱም፡-
FM25 ኮንሶል - በፒ-ኤስ5 እና ሁሉም የኤክስ-ቦክስ ስሪቶት
FM25 ተች - በሊንቴዶ ስዊች
FM25 ሞባይል - በኔትፍሊክስ የሞባይል ጌሞች
FM25 ፒሲ - በፒሲ ፥ በተጨማሪም ለፒሲ ተጫዋቾች ፥ የፉትቦል ማናጀር ድረ-ገጽ ላይ ቅድመ-ትዕዛዝ የተጀመረ ሲሆን ፣ ቀድመው ለሚገዙ የ10% ቅናሽ ተዘጋጅቷል።
የጨዋታ ማለፊያ፡- ለፒሲ እና የኤክስ-ቦክስ የጨዋታ ማለፊያ ተመዝጋቢዎች FM25 ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ፣ የኤክስ-ቦክስ ተጫዋቾች ደግሞ የኮንሶል ሥሪቱን ማግኘት ይችላሉ።
ይህ እትም አዳዲስ በርካታ አስደሳች አማራጮችን የሚያካተት ሲሆን ከእነሱም መካከል ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የሴቶች እግር ኳስ መካተት ፣ የምስል ጥራቱ መሻሻል ፣ እና ልዩ የግጥሚያ ተሞክሮዎች የሚካተቱ ይሆናል። አዲስ ስለሚካተቱ ማሻሻያዎች ከጥቅምት 7 ጀምሮ በይፋ እስከሚለቀቅበት ቀን ድረስ ዝርዝር መረጃዎች በመደበኛነት የሚወጡ ይሆናል።