
ተጫዋቾች 99 ዶላር በመክፈል በኤምቦዲ የተሰራውን ፕሪሚየም የድምፅ አማራጪን መጠቀም የሚችሉ ሲሆን ፣ ይህም አማራጪ በተጫዋቾች የጆሮ ሞርፎሎጂ ላይ በመመርኮዝ የ3ዲ ስፓሻል ድምፅን ያስተላልፋል። ይህ የተሻሻለ የድምፅ አማራጪ እንደ እግር ኮቴዎች ያሉ ጥቃቅን ድምፆችን አጉልቶ ማሰማት የሚችል አዲስ አማራጪ ነው።
ሁሉም የብላክ ኦፕስ 6 ተጫዋቾች የተሻሻለ የጆሮ ማዳመጫ ሞድ ተብሎ የሚጠራውን መሰረታዊ የስፓሻል ድምፅ ስሪትን በነፃ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ፣ ይህም አማራጪ ጥሩ የድምፅ ጥራት የሚሰጥ ቢሆንም በኢምቦዲ ጌምፓክ የቀረበው የማስተካከያ አማራጪ ግን የለውም። አይ! እኔ የዚህን አማራጪ ሙሉ አገልግሎት ማግኘት ነው የምፈልገው የሚሉ ተጫዋቾች ገን ኢመርስ ጌምፓክ የአዘጋጀውን እና የተራቀቀውን ፕሪሚየም ስሪት መግዛት ይችላሉ።
ይህ ጉዳይ በተጨዋቾች ዘንድ ከፍተኛ ክርክርን እና ቅሬታን ያስነሳ ሲሆን ፣ አንዳንድ ተጫዋቾች በአንድ በኩል ፣ ይህ መክፈል ለሚችሉ ሰዎች ፍትሃዊ ያልሆነ ጥቅም የሚሰጥ እና ፣ ነገሩን ተጫወቶ ከማሸነፍ ወደ ከፍሎ ወደ ማሸነፍ እንደሚለውጠው ሀሳባቸውን የገለፁ ሲሆን ፥ በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች ተጫዋቾች ፣ ይህ ጉዳይ ሊጋነን የማይገባው እና የተሻለ ጥራት ያለው የጆሮ ማዳመጫ ከመግዛት የማይተናነስ አማራጭ እንደሆነ በመግለፅ ድጋፋቸውን ገልፀዋል።
የጠላት እንቅስቃሴዎችን መለየት መቻል በድል እና በሽንፈት መካከል ያለውን ልዩነት በሚፈጥሩ እንደ እንደ ኮል ኦፍ ዲውቲ ያሉ ጌሞች ላይ ፣ የድምጽ ጥራት ወሳኝ ሚናን ይጫወታል። ሆኖም ኦንላይን ጌሞች ላይ የተሻሻለ የድምፅ አማራጪን ለመግዛት ጥቃቅን ግብይቶች የመፈፀሙ ጉዳይ የፍትሃዊነት ጥያቄን አስነስቷል።
የኢመርስ ጌምፓክ በስቲም ፣ Battle.net እና ማይክሮሶፍት መደብር በኩል እና ኤክስቦክስ XS ፣ ፕለይስቴሽን እና ፒሲን ጨምሮ በሁሉም የጨዋታ መድረኰች በኩል የሚገኝ ሲሆን ፥ ይህ በ19,99 ዶላር ለአምስት ዓመታት የሚያገለግል አማራጪ ፣ ድምፅ ጋር የተገናኘ በመሆኑ ፣ የጆሮ ማዳመጫዎችን ለሚጠቀሙ ተጫዋቾች ብቻ ጥቅም የሚሰጠው።.
ይህ አማራጪ ወደፊት የጌም ኢንደስትሪው ውስጥ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል ሲሆን ፣ አገልግሎቶችን ለማግኘት የጌም ውስጥ ክፍያ አቀራረብን የሚያንፀባርቅ ጉዳይ ነው። ይህ አካሄድ ወደፊት በሰፊው ተቀባይነት ይኖረው ይሆን ወይም ተገቢ ያልሆነ ክፍያ ተብሎ ይፈረጃል የሚለውን ጊዜ የሚፈታው ጉዳይ ነው።