
ኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 ፣ ጥቅምት 25 ላይ ፒሲ ፣ ፒኤስ4 ፣ ፒኤስ5 ፣ ኤክስቦክስ ዋን ፣ ኤክስቦክስ X/S ላይ የተለቀቀ የዓመቱ ምርጥ ጌም ሲሆን ፣ በብዙ-ተጫዋቾች ሞድ ላይ ተጫዋቾች ሊጠቀሟቸው የሚችሉ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችንም አስተዋውቋል። ይህንንም አስመልክቶ በአፈጻጸም እና በሁለገብነት አኳያ ውጤታማ የሆኑ መሳሪያዎችን መምረጥ እንዲችሉ የሚረዳዎ ዝርዝር መመሪያ አዘጋጅተናል።
እነዚህ መሳሪያዎች በብዙ ተጫዋቾች ሞድን በበላይነት ለመምራት ለሚፈልጉ ተጫዋቾች የሚሆኑ ከባድ እና በጣም አስተማማኝ መሳሪያዎች፦
C9 (አውቶማቲክ ጠመንጃ)
KSV (አውቶማቲክ ጠመንጃ)
XM4 (ጠመንጃ)
AEK-973 (ስናይፐር)
ለተለያዩ ተልዕኮዎች የሚሆኑ የጦር መሳሪያዎች፦
AK-74 (ጠመንጃ)
ሞዴል L (ጠመንጃ)
ጃክል PDW (አውቶማቲክ መትረየስ)
SWAT 5.56 (ስናይፐር)
XMG (ከባድ አውቶማቲክ መትረየስ)
ማሪን SP (ሻት ጋን)
ያላቸውን አቅም በደንብ ፣ ለመጠቀም ልምድን የሚጠይቁ መሳሪያዎች፦
GPMG-7 (አውቶማቲክ ሽጉጥ)
ሳርኮቭ 7.62 (ስናይፐር)
ግሬኮቫ (ሽጉጥ)