icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ኒው ዎርልድ ፡ ኤተርነም ላይ ከፍተኛ ጉዳትን (DPS) ማድረስ የሚያስችሉ መሳሪያዎች 

ኒው ዎርልድ ፡ ኤተርነም ከብዙ የኦንላይን ጌሞች ለየት የሚያደርገው ነገር ፣ የተገደበ ስርዓትን አይከተልም። ይልቁንስ ተጫዋቾች መሳሪያዎችን ፣ ገፀ-ባህሪያትን ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ የጦር መሳሪያዎችን በራሳቸው ምርጫ እና ፍላጎት ማስተካከል ይችላሉ። 

1.መጥረቢያ እና ቀስት (PvP/PvE) 

የመጥረቢያ እና የቀስት ጥምርት ፣ ከርቀት ፈጣን ጥቃቶችን ማድረስ ለሚፈልጉ ተጫዋቾች ተመራጭ ሲሆን ፥ መጥረቢያው እንደልብ እየተንቀሳቀሱ ፈጣን ጥቃቶችን ማድረስ የሚያስችል ሲሆን ፣ ቀስቱ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳቶችን ማድረስ ያስችላል። 

መጥረቢያ 

  • በርዘርክ ትሪ፡- የጉዳት መጠንን ለመጨመር እና ህይዎትን ለማደስ ያገለግላል። 

  • ሬለንትለስ ፊውሪ፡- በጥቃቶች መካከል ያለውን የማገገሚያ ቆይታን በመቀነስ ፣ ይበልጥ የጥቃት የማድረስ ፍጥነትን ለመጨመር ያስችላል። 

ቀስት 

  • ሃንተር ማስተሪ ትሪ፡- ከርቀት የሚደረጉ ውጊያዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳትን ለማድረስ ያስችላል። 

  • ፖይዝን ሻት፡- በጊዜ ሂደት ፣ የጉዳት መጠንን መጨመር ያስችላል። 

ልዩ ብቃቶች 

  • የመጀመሪያ ደረጃ፡- ቅልጥፍና 

  • ሁለተኛ ደረጃ፦ ጥቃቶችን የመቋቋም አቅም 

2.የበረዶ ጓንት እና ጎራዴ (PvP እና የጠላት አለቆች) 

እነዚህ ጥምሮች ከሩቅ እና ከቅርብ ርቀት ለሚደረጉ ውጊያዎች ይጠቅማሉ። የበረዶ ጓንት ከሩቅ ለሚደረጉ ውጊያዎች አንጀት አርስ ሲሆን ፣ ጎራዴው ደግሞ በቅርብ ርቀት ውጊያዎች ወቅት ውጤታማ ያደርጋል። ከሌሎች ተጫዋቾች (PvP) ጋር ለመፋለም ይሁን ከጠላት አለቆች ጋር ለሚደረጉ ውጊያዎች ተመራጪ ናቸው።  

የበረዶ ጓንት 

  • አይስ ቴምፐስት ትሪ፦ ማና ለማደስ እና አካባቢው ላይ የሚገኙ ጠላቶችን ለመቆጣጠር ያስችላል። 

  • አይስ ስቶርም፦ አካባቢው ላይ የሚገኙ ጠላቶች ላይ ጥቃት ለማድረስ እና እንቅስቃሴያቸውን ለመገደብ ወይም እንዲንቀራፈፉ ለማድረግ ያስችላል። 

ጎራዴ 

  • ግሬስ ትሪ፡- ለቅልጥፍና እና ለመልሶ ጥቃት ያገለግላል። 

  • ፍለሪ፡- ከባድ ጉዳትን ማድረስ የሚያስችሉ ፣ ፈጣን ጥምር ጥቃቶችን ለማድረስ ያስችላል። 

 

ልዩ ብቃቶች 

  • አንደኛ ደረጃ፦ ከፍተኛ የድግምት ኃይል 

  • ሁለተኛ ደረጃ፦ ቅልጥፍና እና ጥቃቶችን የመቋቋም አቅም 

3.መስኬት ጠመንጃ እና ጦር (PvP) 

መስኬት ጠመንጃ PvP ላይ ከርቀት ጥቃት ለማድረስ የሚያስችል ሲሆን ፣ ከጦር ጋር ሲጣመር ደግሞ የጠላት ሠራዊቶችን የመቆጣጠር ችሎታን ይሰጣል። 

መስኬት ጠመንጃ 

  • ሻርፕሹተር ትሪ፦ ከርቀት የጠላት አባላትን ዒላማ ውስጥ በማስገባት ጥቃት ለመጣል ያስችላል። 

  • ፓወር ሻት፡- በአንድ ተኩስ ከአንድ በላይ የጠላት አባላትን ተኩሶ መጣል ያስችላል። 

ጦር 

  • ዎፕን ማስተሪ ትሪ፡- አካባቢው ላይ የሚገኙ ጠላቶችን ለመቆጣጠር ያስችላል። 

ልዩ ብቃቶች 

  • አንደኛ ደረጃ፡- ቅልጥፍና 

  • ሁለተኛ ደረጃ፦ ከፍተኛ የድግምት ኃይል ወይም ጥቃቶችን የመቋቋም አቅም 

እነዚህ መሳሪያዎች ምርጥ ከሚባሉት መካከል ቢሆኑም ፣ ጌሙን ሚዛናዊ ለማድረግ በተደጋጋሚ ዝመናዎች ስለሚደረጉ ፡ የጦር መሳሪያ እና የብቃት ምርጫዎትን አዳዲስ በሚወጡ ዝመናዎች መሰረት ምርጫዎትን ማስተካከል አስፈላጊ ነው። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !