
የአማዞን ጌምስ ስሪት የሆነው ኒው ዎርልድ ፡ ኤተረም ልዩ ልዩ ሽልማቶችን እና በቡድን የተዋቀረ ውድድሮችን ያካተተ የመከራ ዝግጅቱን ፣ በሁሉም የጌም መድረኮች ማለትም ፣ በፒሲ ፣ ፒ-ኤስ 5 ፣ ኤክስቦክስ X/S ላይ ሁሉንም ተጫዋቾች በሚያሳትፍ መልኩ አዲስ ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅቷል።
ተሳታፊ ተጫዋቾች በሦስት ቡድኖች የሚከፈሉ ሲሆን እነሱም ፣ Team Mountain, Team Forest, and Team River ተብለው የሚከፈሉ ሲሆን ፥ ተጫዋቾች የፒሲ ፣ የፒ-ኤስ 5 ፣ የኤክስቦክስ X/S ተጠቃሚ ይሁኑ ፣ እያንዳንዱ ቡድን የጋራ ግቦች ለማሳካት በትብብር ተልዕኮዎችን በጋራ መወጣት ይጠበቅባቸዋል።
ቡድኖች በዝግጅቱ ወቅት ከታች የተዘረዘሩትን ተልዕኮዎች ማጠናቀቅ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ፥ የመጀመሪያው ሳምንት ተልዕኮዎች እነዚህን ይመስላሉ፡-
የመጀመሪያውን ተራራ ማስክፈት (ደረጃ 20 ሊደርሱ ይገባል)
ደረጃ 35 መድረስ
የመጀመሪያዎን ቤት መግዛት
መደበኛ የአሰሳ ጉዞን ማጠናቀቅ
የንግድ ክህሎትዎን ወደ ደረጃ 150 ማሳደግ
ዕለታዊ የሂደት ዘገባ፡- በበየቀኑ 7 PM CEST ላይ ይቀርባል።
በቡድን ተልዕኮዎችን መወጣት፡- በቡድን ቢከፋፈሉም ፣ እያንዳንዱ የቡድን አባላት የጋራ ግቦች ለማሳካት በትብብር ተልዕኮዎችን መወጣት ይኖርባቸዋል።
የዝግጅቱ ቆይታ፡- ሶስት ሳምንታት
የብቁነት መስፈርት፡- የዚህ ዝግጅት ተሳታፊ ለመሆን ፣ ተጫዋቾች የመደበኛው ሰርቨር ተጠቃሚ መሆን አለባቸው።
ሽልማቶች፦ ተልዕኮዎችን በአግባቡ ለተወጡ ተጫዋቾች በየሳምንቱ መጨረሻ ሽልማቶች ይበረከታሉ።
ይህ ዝግጅት ፣ በጌም ማህበሩ ዘንድ የኒው ዎርልድ ተወዳጅነት እና ተፈላጊነትን እንደሚጨምር ምንም ጥርጥር የለውም። ከቡድንዎ ጋር በመሆን ተልዕኮዎችን ለመወጣት እና ልዩ ሽልማቶችን ለማግኘት ይዘጋጁ!