icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 ላይ የሚገኙ የXMG ምርጥ አባሪ መሳሪያዎች 

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ኮል ኦፍ ዲውቲ ፡ ብላክ ኦፕስ 6 ፣ ጥቅምት 25 ላይ በፒሲ ፣ ፒኤስ4 ፣ ፒኤስ5 ፣ ኤክስ-ቦክስ 1 እና ኤክስ-ቦክስ X|S ላይ ለጨዋታ በቅቷል። ተጫዋቾችም ተወዳጁን እና ለረጅም ርቀት ውጊያዎች የሚሆነውን XMG መሳሪያ እና የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም በጀብድ የተሞሉ ውጊያዎች ላይ በመሳተፍ ይገኛሉ። ይህንንም አስመልክቶ ተጫዋቾች XMGን እንዴት በአግባቡ እና ከፍተኛ አቅሙን እንዴት አድርገው መጠቀም እንደሚችሉ በዝርዝር የሚገልጽ ፣ መመሪያ አዘጋጅተናል። 

የXMG ጠመንጃ ፣ ውጊያዎችን በድል ለመወጣት በሚፈልጉ ተጫዋቾች ዘንድ ተመራጭ የሆነ መሳሪያ ሲሆን ፣ አፈፃፀሙን ይበልጥ ከፍ ለማድረግ የሚረዱ አባሪዎችን ቀጥለን አስቀምጠናል። 

መደበኛ አባሪዎች፡- 

  • አፈሙዝ፡- ማፈኛ (ደረጃ 16) 

  • ሳንቃ፡- ረጅም ሳንቃ (ደረጃ 9) 

  • ሠደፍ፡- Infiltrator Stock (ደረጃ 3) 

  • ሳንቃ ስር ተለጣፊ፡- Vertical Grip (ደረጃ 4) 

  • የኋለ እጀታ፡- Express Grip (ደረጃ 8) 

ተጨማሪ አባሪዎች፡- 

  • ሠደፍ፡- Infiltrator Stock (ደረጃ 3) 

  • የኋለ እጀታ፡- Express Grip (ደረጃ 8) 

  • ሳንቃ ስር ተለጣፊ፡- Ranger Grip (ደረጃ 26) 

  • የአተኳኮስ ዓይነት፦ የተኩስ እርግጫን የሚቋቋም ስፕሪንግ (ደረጃ 33) 

  • ካርታ፡- Fast Mag II (ደረጃ 18) 

 

ተጨማሪ ጠቃሚ መሳሪያዎች 

ከXMG በተጨማሪ ውጊያዎች ላይ ፣ እንደ C9 ያሉ አውቶማቲክ ሽጉጦችን ወይም ለቅርብ ርቀት ውጊያ የሚያገለግለውን Jackal PDW ጩቤ ፣ እና ብዙ ጠላቶችን በአንድ ጊዜ ማውደም የሚያስችልዎትን ተለጣፊ ቦምብ መታጠቅ ይበልጥ ውጤታማ ያደርግዎታል። በተጨማሪም ፣ Assassin ፣ Rush እና No Sprint በመጠቀም ፣ የመንቀሳቀስ እና ዱካ የማፈንፈን ችሎታዎችዎን ይበልጥ ማሳደግ ይችላሉ። Joker Overkillንም በማካተት የተለያዩ የጥቃት አማራጮችን ማግኘት ይችላሉ። 

ያስታውሱ! ከላይ የዘረዘርናቸው አባሪዎች እንደየሁኔታው ሊለዋወጡ ስለሚችሉ ፣ ከእርስዎ አጨዋወት እና ምርጫ ጋር ይሄዳል ብለው የሚያስቧቸውን በመቀነስ ወይም በመጨመር ፣ ማስተካከል ይችላሉ። በመጨረሻም ፣ የብላክ ኦፕስ 6 የጨዋታ ማለፊያ ያላቸው ተጫዋቾች ፣ ጨዋታቸውን ይበልጥ አስደሳች የሚያደርጉ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ፣ የመሳሪያ ማሳመሪያዎች እና የተለያዩ አማራጮች ተዘጋጅተው ይጠብቋቸዋል።  

መልካም ጨዋታ! 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !