
ታዋቂው የኦንላይን ጌም ኒው ዎርልድ ሀ ብሎ ከተጀመረ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ፥ አሁን ደግሞ የኒው ዎርልድ አዲስ ቅጥያ የሆነውን ፣`ኒው ዎርልድ ፡ ኤተርነም ፣ ከጥቅምት 15 ጀምሮ ተጫዋቾችን በአዳዲስ ተልዕኮዎች እና ዕድሎች ወደተሞላችው ወደ ኤተርነም ደሴት በመውሰደ ላይ ይገኛል። በ2024 የጌሞች ፌስት ላይ የተዋወቀው ይህ ቅጥያ ራሱን ከቻለ አዲስ ጌም ያልተናነሰ ትልቅ ዝማኔ እንደሆነም ብዙ ተነግሮለታል።
ኤተርነም ደሴት ውስጥ ለአደን ከሚሆኑ በርካታ ፍጥረታት መካከል ፣ ስፖርባክ ከርከሮዎች ሲሆን ስጋቸውን ለምግብነት መጠቀም በሚፈልጉ ወይም የብርቅዬ ሀብቶች አዳኝ በሆኑ ጀብደኛ ተጫዋቾች ዘንድ ዋነኛ ኢላማዎች ናቸው። እነዚህ ከርከሮዎች በዋነኝነት በተወሰኑ አካባቢዎች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ፣ እነዚህን ብርቅዬ ፍጥረታት የት እና እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ በዚህ መመሪያ እናያለን።
እነዚህን ፍጥረታት ሊያገኙባቸው ከሚችሉባቸው አካባቢዎች አንዱ በኤሊሲያን ግዛት ውስጥ በሚገኘው ስኬልክሊፍ በተባለው ለምለም እና ፈታኝ ቦታ ሲሆን ፥ ስፍራው በተለያዩ ሀብቶች እና የዱር አራዊት የተሞላ በመሆኑ ለአዳኞች ምቹ እና ተመራጪ የአደን ክልል ነው። ይህን ቦታ በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ እና ፍለጋዎን ቀላል ለማድረግ ከስር ያስቀመጥነውን የኒው ዎርልድ ፡ ኤተርነም ካርታ ይመልከቱ፦
ድል ቀንትዎት ይህን እንስሳ አድነው መጣል ከቻሉ ፣ ብርቅዬ እና ውድ የሆኑ ሀብቶችን ማግኘት እንዲችሉ ቆዳውን መግፈፍዎን ያስታውሱ። ይህም ምግብ ለማዘጋጀት ፣ አዲስ መሳሪያዎችን ለመሥራት ወይም ለሌሎች ተጫዋቾች አትርፈው እንዲሸጡ ያስችሎታል።
መልካም አደን!!