
ኢሻ Arcane ምዕራፍ 2 ክፍል 2 (Watch It All Burn) ላይ ለመጀመርያ ጊዜ የታየች ገፀ-ባህሪ እና ዛዩን ውስጥ የምትኖር መናገር የተሳናት ወላጅ አልባ ህፃን ነች። በኬም-ባሮን ክሮስ እና ስሜክ የተላኩ ወሮበሎችን ለማምለጥ በምትሞክርበት ወቅትም ነበር ከጂንክስ ጋር የተገናኙት ፣ ጂንክስም ከወሮበሎቹ ካዳነቻት በኋላም ነበር ፣ ተከታዩዋ ለመሆን የወሰነችው።
ኢሻም ከጂንክስ ጋር ያለትን ግንኙነት በማጠንከር ምዕራፍ 1 ላይ በሲልኮ እና በጂንክስ መካከል የነበረው ዓይነት ትስስርን መፍጠር የቻሉ ሲሆን ለየት የሚያደርገው ነገር አሁን ጂንክስ የጠባቂ ሚናን መውሰዷ ነው። ጂንክስ ከተማው ውስጥ አሉ ከሚባሉ ወንጀለኞች ቀንደኛዋ ብትሆንም ፣ ይህ ጂንክስን ከመከተል እና ራሷን አደጋ ውስጥ ከማስገባት ኢሻን አላስቆማትም። በክፍል 3 ላይም በቪ እና ጂንክስ መካከል በተፈጠረው እሰጣገባ ውስጥ ጂንክስን ለመርዳት ህይወቷን በማያወላውል ሁኔታ አደጋ ላይ ስትጥል ይታያል።
መናገት-የተሳናት ብትሆንም ፣ የኢሻ ገፀ-ባህሪ ጥልቅ ስሜትን የሚፈጥር እና ጂንክስ ያለፈ ታሪኳን እንድታስታውስ እና ወንጀለኛነቷን ወደ ጎን በማድረግ ፣ የአሳዳጊነት እና የጠባቂ ሚናን እንድትጫወት እና ፣ ሌላ ጎኗ እንዲታይ አድርጓል። ይህ ጥብቅ ግንኙነታቸውን የምዕራፍ 2 ማጀቢያ የሆነው እና በኢሶን ቻን የተሰራው የኢሻ ዘፈን ላይ ለማሳየት ተሞክሯል። በሙዚቃ ቪዲዮም ላይ ጂንክስ እና ኢሻ ከተማው ውስጥ ሲሯሯጡ እና ሲተቃቀፉ ያሳያል።
ኢሻ Arcane ላይ የተፈጠረች ኦሪጅናል ገፀ-ባህሪ በመሆኗ ፣ League of Legends ላይ አትገኝም። ይሁን እንጂ አድናቂዎቿ እንደ ቴሞ እና ጃና መጪዋ ሻምፒዮን ልትሆን እንደምትችል ይገምታሉ። አንድ ታዋቂ ንድፈ ሃሳብ ከስሟ ትርጉም በመነሳት እንደሚጠቁመው ኢሻ ማለት አምላክ ወይም ጠባቂ ማለት በመሆኑ እና ጂንክስን የመጠበቅ ባላት ሚና ምክንያት ፣ ኢሻ የዛውን ጠባቂ አምላክ ጃና ልትሆን እንደምትችል ይጠቁማል።
የምዕራፍ 2 ክፍል 6 መጨረሻ የኢሻን የወደፊት እጣ ፈንታ አጠራራሪነት አሳይቷል። በአስደናቂ ሁኔታ ፣ ጂንክስን ከቫንደር ለማዳን ስትል እራሷን መስዋዕት ስታደርግ ምዕራፍ 2 ክፍል 6 ላይ ታይታለች። እስካሁን መጨረሻዋ ምን ሊሆን እንደሚችል በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም ፣ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ልትሞት እንደምትችል በኢሻ ዘፈን ግጥሞች ላይ እና ከሙዚቃው ቪዲዮ መረዳት ይቻላል።