icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

የአርኬኗ ገፀ-ባህሪ አማራ እና የጥቁር ሮዝ ድብቅ ዓላማ! 

የአርኬን ምዕራፍ 2 የፒልቶቨሯን ባላባት እና ከውበቷ በስተጀርባ ድብቅ አጀንዳዎች የምታራምደውን የአማራን ገፀ-ባህሪ ያስተዋውቃል። አማራ የድብቁ የጥቁር ሮዝ አባል ስትሆን ፣ ይህም ቡድን ከትዕይንቶች በስተጀርባ የሚሰራ ኃይለኛ እና ምስጢራዊ ቡድን ነው። 

አማራ ባለ-ግራጫ ፀጉር እና የተዋበ መልክ ያላት የነጋዴዎች አውራ ብቻ ሳትሆን ፣ የድብቁ ጥቁር ሮዝ ቡድን ድብቅ አባልም ነች። ውብ መልኮቿ ፣ ድብቅ እና አስማታዊ አጀንጃዎቿን ማስፈፀሚያ ጭምብሎቿ ሲሆኑ ፥ አስማታዊ ችሎታዎቿን እና የማጭበርበር ስልቶቿን በመጠቀም ፣ የፒልቶቨር ፖለቲካ እንድትቆጣጠር ፣ በሄክስቴክ ዙሪያ ከአማካሪዎች ጋር ስልታዊ ድርድሮችን በማድረግ ውሎችን እንድትፈጽም ያስችሏታል። 

አድናቂዎች ስለ አማራ መላ ምቶች ያሏቸው ሲሆን ፣ የመጀመሪያው አማራ የሊ`ብላንክ የላብራቶሪ ድቅል ናት የሚል ሲሆን ፣ ሁለተኛው ደግሞ የጥቁር ሮዝ ቀጥተኛ ተወካይ ወይም ከፍተኛ ደረጃ ተመልማይ ነች የሚል ነው። ፊቷ ላይ የሚገኘው ምልክት እና አስማታዊ ችሎታዎቿ ከዚህ ምስጢራዊ ድርጅት ጋር ጥልቅ ግንኙነት እንዳላት የሚያሳዩ ግልጽ ምልክቶችም ናቸው። 

የአማራ ጉዞ ከአምበሳ ሜዳርዳ ጋር በተፈጠረ ግጭት የሚቋጭ ሲሆን ፥ በዚህ ግጭት ከፍተኛ አቅም ቢኖራትም አማራ ልትሸነፍ ችላለች። ከመሞቷ አፍታዎች በፊት “መሞቴ ምንም ማለት አይደለም” የሚል ምስጢራዊ መልክት ያስተላለፈች ሲሆን ፥ ይህ ምስጢራዊ መልዕክትም ፥ እሷ ብትሞትም የጥቁር ሮዝ እቅዶች እንደሚቀጥል መጠቆሚያ ነው። 

አማራ ብዙ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን ያስነሳች ገፀ-ባህሪ ስትሆን፦  

  • የጥቁር ጽጌረዳ ዓላማ ምንድን ነው? 

  • ምን ያህል የሚሆኑ የጥቁር ሮዝ አባላት ፥ በፒልቶቨር በድብቅ እየሰሩ ይገኛሉ? 

  • የአማራ መሞት ምን ሊያስከትል ይችላል? 

የአማራ አጭር ግን ተፅዕኖ ፈጣሪ ቆይታ ፥ የአርካንን አስደናቂ ገፀ-ባህሪያትን እና ጥልቅ ታሪኮችን የመፍጠር ብቃትን የሚያሳይ ነው። ስለ ጥቁር ሮዝ እና ድበቅ ዓላማዎቹ በቅርቡ የምናውቅ ይሆናል። 

 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !