
Call of Duty: Black Ops 6 ጥቅምት 25 ፣ 2024 ፥ ፒሲ ፣ ፒኤስ-4 ፣ ፒኤስ-5 ፣ ኤክስ-ቦክስ 1 እና ፣ ኤክስ-ቦክስ X/S ላይ ለጨዋታ የበቃ ሲሆን ፣ የተለያዩ አስደናቂ ተልዕኮዎችን እና በፈታኝነታቸው የሚታወቁትን "Secret Operations" ተልዕኮዎች በውስጡ አካቷል። ከእነዚህ ተልዕኮዎች አንዱ የሆነው "Hard Breakup" የበርካታ ተጫዋቾችን ትኩረት መሳብ ችሏል። በዚህ ተልዕኮ ወቅት 7 ድብቅ ጥቃቶችን መሠንዘር የሚጠበቅብዎ ሲሆን ፥ እጅግ ትዕግስትን ፣ እና ስልታዊ አካሄድን የሚጠይቅ ተልዕኮ በመሆኑ ለብዙ ተጫዋቾች እጅግ ፈታኝ ሆኗል። ይህንን ተልዕኮ በቀላሉ ለመወጣት ይረዳዎት ዘንድ አንዳንድ ጠቃሚ ነጥቦችን እንደሚከተለው አዘጋጅተናል፦
ይህ ተልዕኮ ስልትን እና አድፍጦ ማጥቃትን የሚጠይቅ በመሆኑ እና አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን ለማስወገድ ፥ ቅንብሮችዎን ማስተካከል ይገባዎታል።
"Combat" አማራጭ ስር የሚገኘውን "Advanced Combat Settings" ይክፈቱ።
"Human Shield/Execution" የሚለውን አማራጭ ወደ "Execution Only" ይቀይሩ።
ይህም አድፍጠው ጥቃቶችን በሚሰነዝሩ ወቅት አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን ወይም ኮሽታዎችን እንዲያስወግዱ ይረዳዎታል።
Ninja፡- ኮቴዎን በማጥፋት ፣ ድብቅ ጥቃቶችን እንዲጥሉ ያስችልዎታል።
Tracker፡- የጠላት ዱካዎችን በቀላሉ ለማነፍነፍ ፣ እና ያሉበትን ለማወቅ ይረዳል።
Awareness፡- አካባቢዎ ላይ የሚገኙ ጠላቶችን ድምጽ በደምብ መስማት እንዲችሉ ፣ እና ራስዎን ከአደጋ ለማዳን ይረዳዎታል።
መሳሪያዎች
Tactical Insertion፡- ከጠላት ጀርባ በሚገኙ ስልታዊ ቦታዎች ላይ ህይዎትዎን እንደገና ለማስጀመር ያስችላል።
የጭስ ቦምቦች፦ ከጠላት በመሰወር እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ እና ጠላት ባልጠበቀው ሁኔታ ጥቃት ለማድረስ የሚጠቅም መሳሪያ ነው።
ስልታዊ እንቅስቃሴን የሚፈቅዱ የጌም ሞዶችን ይምረጡ፡-
እንደ Hardpoint ያሉ ሞዶች ፣ ህይዎትን ድጋሚ ማስጀመሪያ ነጥቦቹ ቋሚ በመሆኑ ጥሩ አማራጭ ሲሆን ፥ ይህም ግርግር ውስጥ ሳይገቡ በድብቅ ጥቃቶችን መጣል ያስችልዎታል።
ያስታውሱ! ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርነው ይህን ተልዕኮ ለመወጣት 7 ድብቅ ጥቃቶችን መሠንዘር የሚጠበቅብዎ በመሆኑ ፣ በመጀመሪያ ሙከራዎ ባይሳካልዎት ፣ ተስፋ እንዳይቆርጡ! Black Ops 6 ሰፊ የጦር መሳሪያዎች እና የቦታ ምርጫዎችን ከማቅረቡም በላይ ጌም ፓስ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ፥ ይህን ተልዕኮ ለመወጣት የሚያስችልዎትን ፣ ስልታዊ ሂደቶችዎን እና አጨዋወትዎን ማሻሻል የሚችሉበት ብዙ እድሎችን ይሰጣል።
መልካም ጨዋታ!