
Call of Duty: Black Ops 6 ጥቅምት 25 ቀን የተለያዩ አስደናቂ ተልዕኮችን በማካተት ለጨዋታ የበቃ ሲሆን ፣ መሳሪያዎች ላይ ከሚያተኩሩ ተልዕኮች መካከል አንዱ የሆነው ተጫዋቾች ለጩቤዎቻቸው የተለያዩ ካሞዎችን የማስከፈት ተልዕኮ ሲሆን ፣ በዚህ መመሪያ በብዙ-ተጫዋቾች ፣ በዞምቢዎች እና በዋር ዞን ሞዶች ላይ በመሳተፍ እንዴት የጩቤ ካሞዎችን ማስከፈት እንደሚቻል በዝርዝር እናያለን።
የብዙ-ተጫዋቾች ሞድ ላይ የጩቤ ካሞዎችን ለማስከፈት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟሉ፦
Special 1፡- ጩቤ በመጠቀም 100 ጠላቶችን ማስወገድ
Special 2፡- Enforcer perk በመጠቀም 50 ጠላቶችን ማስወገድ
Special 2፦ ምንም ጉዳት ሳይደርስብዎ 30 ጠላቶችን ማስወገድ
Gold፦ 10 ጊዜ ሁለት ጠላቶችን በአንዴ ማስወገድ
Diamond፡- ሳይሞቱ በተከታታይ 10 ጊዜ 3 ጠላቶችን በአንዴ ማስወገድ
Black Vertebrae፦ በተከታታይ 3 ጊዜ ሶስት ጠላቶችን ማስወገድ
Dark Matter፡- ሳይሞቱ በተከታታይ 3 ጊዜ 5 ጠላቶችን ማስወገድ
የዞምቢዎች ሞድ ላይ የጩቤ ካሞዎችን ለማስከፈት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟሉ፦
Military፦ 2000 ጠላቶችን ማስወገድ
Special 1፡- Brain Rot effect በመጠቀም 300 ጠላቶችን ማስወገድ
Special 2፡- 75 ታጣቂ ዞምቢዎች ማስወገድ
Mystic Gold፦ በተከታታይ 10 ጠላቶችን 15 ጊዜ ማስወገድ
Opal፡- 30 ልዩ ዞምቢዎችን ማስወገድ
Post Mortem፡- በተከታታይ 20 ጠላቶችን 10 ጊዜ ማስወገድ
Nebula፡- 10 የዞምቢ ቁንጮዎችን ማስወገድ
የዋርዞን ሞድ ላይ የጩቤ ካሞዎችን ለማስከፈት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟሉ፦
Military፦ ጩቤ በመጠቀም 100 ጠላቶችን ማስወገድ
Special 1፡- (መስፈርቱ እስካሁን አልታወቀም)
Special 2፡- (መስፈርቱ እስካሁን አልታወቀም)
Golden Tiger፡- (መስፈርቱ እስካሁን አልታወቀም)
King’s Ransom፡- (መስፈርቱ እስካሁን አልታወቀም)
Catalyst፡- (መስፈርቱ እስካሁን አልታወቀም)
Abyss፡- (መስፈርቱ እስካሁን አልታወቀም)
በሁሉም ሞዶች ላይ ያሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጩቤ ኮሞዎችን ማስከፈት እና ብቃትዎን ማስመስከር ይችላሉ!