
Pokémon TCG Pocket በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጫዋቾችን ማስደሰቱን የቀጠለ ሲሆን ፣ አሁን ደግሞ በጉጉት ሲጠበቁ የነበሩ ተከታታይ ዝመናዎችን ለመተግበር ዝግጅት ላይ ነው። በአንድ ሳምንት ውስጥ 30 ሚሊዮን ዳውንሎዶች እና ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ካስገቡ በኋላ አስደሳች አዳዲስ መረጃዎች ይፋ አድርገዋል።
አዳዲስ ቡስተሮች ከ ታህሳስ ፣ 2024 ጅምሮ የሚለቀቁ ሲሆን
A1a ጥቅል፡- ታህሳስ 16 ፣ 2024 ይጀመራል።
A2 ማስፋፊያ፡- ጥር 29 ፣ 2025 ይጀመራል።
እነዚህ ተጨማሪ የቡስተር ጥቅሎች አሁን ላይ ከሚገኙት ፥ የጀነቲክ ኤፔክስ ፣ ሜውትዎ ፣ ቻሪዛርድ እና ፒካቹን ቡስተሮችን የሚቀላቀላሉ ይሆናል።
ከጥር 2025 ጀምሮ ተጫዋቾች የተመረጡ ካርዶችን መገበያየት ይችላሉ።
አሁን ላይ ለግብይት የሚቀርቡ ካርዶች የተወሰኑ ቢሆኑም በጊዜ ሂደት ግን የሚጨመሩ ይሆናል።
ይህ ጌም አስገራሚ ዓለም አቀፍ ስኬቶችን ማግኘት የቻለ ሲሆን ፣ 50% የሚሆነውን የገቢ መጠን ከጃፓን እንዲሁም ፥ 25% የሚሆነውን ደግሞ ከአሜሪካ ማግኘት ችሏል። ይህን ተከትሎም አዘጋጆቹ በቅርቡ አዳዲስ የጨዋታ ሞዶችን እና አማራጮችን በቅርቡ ለተጫዋቾች እንደሚያደርሱ ቃል ገብተዋል።
ለማስታወስ ያህል ፣ Pokémon Trading Card Game Pocket ፥ ታዋቂው የፖክሞን ካርድ ጨዋታን መሠረት በማድረግ በCreatures Inc. እና DeNA ተዘጋጅቶ በPokémon ኩባንያ የታተመ የሞባይል ጌም ሲሆን ፥ iOS ፣ macOS እና Android ላይ ይገኛል።
Pokémon TCG Pocket መስከረም 26 ፣ 2024 በኒውዚላንድ ተጀምሮ ፣ ህዳር 30 ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትን ማግኘት ችሏል። ተጫዋቾች በየቀኑ የካርድ ጥቅሎችን እንዲከፍቱ ፣ ዴኮችን እንዲፈጥሩ ፣ ኦንላይን ላይ ወይም ለብቻቸው ውድድሮች ላይ እንዲሳተፉ እና ስብስቦቻቸውን እንዲያሰፉ የሚያስችል ጌም ነው።
Pokémon TCG Pocket ያስመዘገባቸው ስኬቶች፡-
አስር ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 30 ሚሊዮን ዳውንሎዶች።
በተመሳሳይ ጊዜ 12 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገቢ።
ጃፓን 45% የሚሆነውን የገቢ ድርሻ ስትይዝ ፥ ዩናይትድ ስቴትስ 25% የሚሆነውን የገቢ ድርሻ ትይዛለች።
Pokémon TCG Pocket ለመጫወት ቀላል የሆነ ፣ የፖክሞን አድናቂዎች የድሮ ትዝታዎችን እንዲያጣጥሙ የሚያስችል እና የካርድ ጨዋታዎችን ለሚወዱ ሁሉ የሚሆን ምርጥ ጌም ነው።
በተደራሽነት ባለው የጨዋታ አጨዋወት ስርዓት እና በሚቀሰቅሰው ናፍቆት፣ Pokémon TCG Pocket እራሱን ለካርድ ጨዋታ አፍቃሪዎች እና ለፖክሞን አድናቂዎች የማዕዘን ድንጋይ አድርጎ እያስቀመጠ ነው።