
Pokémon TCG Pocket በ2024 ጥቅምት ወር ላይ ለጨዋታ ከበቃ አንስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ዓለም-አቀፍ አድናቂዎችን ማፍራት የቻለ ጌም ቢሆንም ፣ አንድ የሚጎድለው ነገር እንዳለ ተጫዋቾች ቅሬታቸውን አቅርበዋል! ቅሬታውን ያስነሳው ጉዳይም ጨዋታውን ፍትሃዊ ፣ አፎካካሪ ፣ እና ይበልጥ አስደሳች ሊያድርግ የሚችለው ፣ የደረጃ ሠንጠረዥ አማራጭ Pokémon TCG Pocket ላይ አለመኖሩ ነው።
የPvP ውድድር ሂደቱ የደረጃ ሠንጠረዥ አማራጭን ባለማካተቱ ፥ እንደ Mewtwo/Gardevoir ያሉ የተለመዱ ስልቶች ውድድሮችን የመቆጣጠር አቅማቸው ከሌሎች ከፍ ማለት እና ፤ አዳዲስ ተጫዋቾችን ከፍተኛ ልምድ ካላቸው ተጫዋቾች ጋር የማዛመዱ ጉዳይ ጨዋታውን ሚዛናዊ ያልሆነ እና ኢ-ፍትኃዊ አድርጎታል። ለዚህም መፍትሄ ሊሆን የሚችለው የደረጃ ሠንጠረዥ አማራጭ ሲሆን የዚህ አማራጭ መካተት ፍትሃዊ ውድድሮችን ለማድረግ ፣ ተጫዋቾችን በደረጃ እንዲመደቡ እና ተመጣጣኝ ሽልማቶችን ማግኘት እንዲችሉ ያስችላል።
ምንም እንኳን አዘጋጆቹ ስለደረጃ ሠንጠረዡ በይፋ ያሉት ነገር ባይኖርም ፣ በቅርቡ ሊካተት እንደሚችል አንዳንድ ጭምጭምታዎች ተሰምተዋል። ከእነዛም መካከል Tiky የተባለው ፈረንሳዊ Streamer ይህ አማራጭ ህዳር 7/2024 እ.ኤ.አ. ሊካተት እንደሚችል ጥቆማ የሰጠ ሲሆን ፣ የተለያዩ መረጃ ፈልፋዮችም የጌሙ ፋይሎች ውስጥ የ"የደረጃ ሠንጠረዥ ሞድ" የሚል ማጣቀሻ ማግኘታቸውን አሳውቀዋል። በተጨማሪም አዘጋጆቹ ጋር በተደረገ ቃለ-መጠይቅ ፥ የተጫዋቾችን አስተያየት በመቀበል እና ግምት ውስጥ በማገባት የስራ ሂደት ላይ እንደሆኑ ገልፀዋል።
ከላይ እንደጠቀስነው ምንም የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም ፣ የደረጃ ሠንጠረዥ ሞዱ ቀጥሎ የተዘረዘሩን ሊያካተት ይችላል፡-
የደረጃ ምድቦች (ነሐስ ፣ ብር ፣ ወርቅ ፣ እና ማስተር)
የተጫዋቾችን ደረጃ መሠረት ያደረጉ ሚዛናዊ እና ፍትሃዊ ግጥሚያዎች
እንደ ቡስተር ፣ ልዩ ካርዶች ወይም ማስጌጫዎች እና የዴክ ገደቦች
ይህ የደረጃ ሠንጠረዥ ሞድ ፣ ታህሳስ 2024 ከሚለቀቁት አዳዲስ ቡስተሮች ፣ ጥር 2025 ከሚደረገው የካርዶች ሽያጭ እና ጌሙ ውስጥ ከሚደረጉ ልዩ ዝግጅቶች ጋር አብሮ ሊለቀቅ እንደሚችል ይገመታል።
ለአሁኑ ተጫዋቾች ለደረጃ ሞድ ለመዘጋጀት ዴኮቻቸውን እና ስልቶቻቸውን ማሻሻል ላይ ማተኮራቸውን መቀጠል ይችላሉ። ይህ አማራጭ በአግባቡ ከተተገበረ Pokémon TCG Pocket ከአንጋፋ እና ምርጥ የሞባይል ካርድ ጌሞች ጎራ እንዲመደብ ያስችለዋል።