
የሜል እናት የሆነችው እና ፒልቶቨር ካውንስ ውስጥ ቁልፍ የሆነችው የኖክሰሷ ርህራሄ አልባዋ አምበሳ ሜዳርዳ ፣ አዲሷ ሻምፒዮን በመሆን League of Legendsን ልትቀላቀል ነው። በArcane ምዕራፍ 1 ላይ ባሳየችው አጭር ግን ተፅዕኖ ፈጣሪ ትዕይንቶች የምትታወቀው አምበሳ ሜርዳድ በመጪው ተከታታይ የውድድር ዘመን ጉልህ ሚናን የምትጫወት ይሆናል። የአምበሳ ሜርዳድን በአዲሱ ምዕራፍ መካተት በብዙዎች በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ክስተት ሲሆን ፣ አሁን ሰዓቱ ደርሶ የታላቁን K'Santeን ብቃቶች የሚያስንቁ ወደር የለሽ ብቃቶቿን እና ሁለገብነቷን ይዛ ለመምጣት ቀጠሮ ይዛለች።
አምበሳ ሜርዳድ PBE ሰርቨር ላይ ረቡዕ ፣ ህዳር 6 ፣ 2024 League of Legendsን እንደምተቀላቀል የተረጋገጠ ሲሆን ፥ ከቀኑ በፊት ብቃቷን አስቀድመው አይተው መመስከር የሚፈልጉ ከሆነ ፣ ከዚህ በታች የሚገኘውን ቪዲዮ መመልከት ይችላሉ።
አምበሳ በጦርነት ተከባ ነበር ያደገችው። ገና አሥር ዓመት ሲሞላት ነበር ፣ አባቷ ወደ ሂልድናርድ የጦር ሜዳ የወሰዳት። እዚያም ከሞቱ እና ከቆሰሉ ወታደሮች የጦር መሣሪያዎችን ይዘርፉ ነበር። ይህ እና በሞት የተከበበ አስተዳደጓ ዛሬ ውስጧ ላይ ለሚፈነጨው ጭካኔ እና በእሳት የተፈተነ ተዋጊ ማንነቷ ትልቅ ሚናን ተጫውተዋል።
ጎልማሳ ከሆነች በኋላ እና ልጆች ከወለደች በኋላም ፣ ይህን ማንነቷን ልጆቹዋ ላይ ለማስረጽ ብትሞክርም ፣ ልጆቿ ከሷ ፍፁም የተለየ መንገድን መርጠዋል። ወንድ ልጇ ኪኖ በሰላም የሚያምን ሲሆን ፣ ሴት ልጇ ሜል ደግሞ ጦርነትን እንደ መጨረሻ አማራጭ የምትመለከት ሆነች። ይህም በመኃላቸው ከፍተኛ ልዩነትን ቢፈጥርም ፣ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ሊያጠነክረው ችሏል።
አምበሳ ሜዳርዳ በ Arcane ምዕራፍ 2 ውስጥ ታላቅ ሚናን ትጫወታለች። በተለይም ከሴት ልጇ ሜል ጋር ያላት የተወሳሰበ ግንኙነት ትልቅ ድርሻን ይይዛል። በተጨማሪም ፣ በፒልቶቨር እና ዛውን መካከል እየጨመረ ለሚመጣው አለመግባባት እና ውጥረት ፣ ወደ ጦርነት እንዲያመራም ትልቁን ሚና የምትጫወት ይሆናል።
ለአምበሳ ሜዳርዳ ዝግጁ ነዎት? መልካም ጨዋታ!