
Call of Duty: Black Ops 6 ጥቅምት 25 ፣ 2024 ፥ ፒሲ ፣ ፒኤስ-4 ፣ ፒኤስ-5 ፣ ኤክስ-ቦክስ 1 እና ፣ ኤክስ-ቦክስ X/S ላይ ለጨዋታ በቅቷል። አሁን ደግሞ በምዕራፍ 1 ፣ ለቡድን-ጨዋታ ሞድ እና ለዞምቢ ሞድ አድናቂዎች አስደሳች ዝመናዎችን ለማምጣት ዝግጅቱን በመጨረስ ላይ ይገኛል። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ብዙ ተጫዋቾች እነዚህ አዳዲስ ማሻሻያዎች መቼ እንደሚለቀቁ ለማወቅ ጉጉት ላይ የሚገኙ ሲሆን ፥ እኛም ምን አዳዲስ ዝማኔዎች እየመጡ እንደሆነ እና መቼ እንደሚለቀቁ በዝርዝር አዘጋጅተናል።
ህዳር 14 አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ የBlack Ops 6 የመጀመሪያው ዋና ዝመና ፣ የዞምቢዎች ሞድ ላይ አዳዲስ አስደሳች ማሻሻያዎችን ያስተዋወቃል። Krig C እና Saug የተባሉ ሁለት አዳዲስ መሳሪያዎች የሚካተቱ ሲሆን ፥ ሃንድ ካነን ፥ ተርሚነስ እና ላይቤሪቲ ፎልስም ልዩ ማሻሻያዎችን ያስተናግዳሉ። በተጨማሪም ተጫዋቾች ስልቶቻቸውን ማስፋት የሚያስችሏቸው ሶስት አዳዲስ በብልገሞችን ማግኘት የሚችሉ ይሆናል።
ሌላው ደግሞ አዳዲስ ሽልማቶች ፣ ውጊያ ማሻሻያዎች ፣ የተለያየ ይዘት ያላቸው የጥይት ካርታዎች ፣ አዲስ የጠላት ዓይነቶች እና ሌሎች የተለያዩ ማሻሻያዎች በጊዜ ሂደት የሚካተቱ ይሆናል። እነዚህ ማሻሻያዎች የሚለቀቁበት ትክክለኛ ቀን በይፋ ያልተገለፀ ቢሆንም ፣ የተወሰኑት የምዕራፍ 1 አጋማሽ ዝማኔ ጋር ወይም ታህሳስ 12 አካባቢ አብረው ሊለቀቁ ይችላሉ፣።
በዚህ የምዕራፍ 1 አጋማሽ ዝማኔ ላይ ፣ the Citadel of the Dead የተባለ አዲስ አካባቢ ለሁሉም ተጫዋቾች የሚከፈት ሲሆን ፥ ከአካባቢው መጠሪያ ስም በመነሳት ፣ ድቅድቅ ጨለማ እና አስፈሪ ቤተ-መንግስት ውስጥ የሚደረግ እጅግ መሳጭ እና ልብ ሰቃይ ከዞምቢዎች ጋር የሚደረግ እልህ አስጨራሽ ውጊያን ይዞ እንደሚመጣ ይጠበቃል።
ህዳር 14 በጉጉት ለሚጠብቁት አድናቂዎቹ የሚደርሰው ፣ የCall of Duty: Black Ops 6 ምዕራፍ 1 ፥ ከመቸውም በላይ አስደናቂ እና አስደሳች ይዘቶችን ይዞ እንደሚመጣም ጥርጥር የለውም!
መልካም ጨዋታ!