icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ተወዳጁ የCall of Duty Black Ops 6 ትራንዚት ካርታ መውጫ ቀን 

ዞምቢስ ሞድ ላይ በጣም ታዋቂ እና ተወዳጅ ከሆኑ ካርታዎች አንዱ የሆነው የትራንዚት ካርታ ፥ Black Ops 2 ላይ በድጋሚ ይመለሳል አይመለስም የሚለው ጥያቄ በተጫዋቾች ዘንድ ትልቅ ጉጉትን አሳድሯል። ይህ ጥያቄም በተጫዋቾች ዘንድ እንዲነሳ ያደረገው ምክንያት ትራንዚት ላይ ተወዳጅ የሆነው የአውቶቡስ ሹፌር ገፀ ባህሪ ፣ Black Ops 6 Prestige 6 ላይ መልኩ ባጆች ላይ በመታየቱ ነው። 

የInsider Gaming ቶም ሄንደርሰንም ፣ በጌሙ የጨዋታ ሙከራ ላይ የተሳተፉ ተጫዋቾች ትራንዚትን መሰል ካርታ መመልክታቸውን በመዘገብ የሚናፈሰው ወሬ ላይ ነዳጅ ጨምሮበታል። Activision ስለዚህ ጉዳይ በይፋ ምንም ያለው ነገር ባይኖርም ፣ በአንዳንድ ፍንጮች መሠረት ፣ በአዲስ መልክ የተሻሻለ የትራንዚት ካርታ ድጋሚ ሊካተት እንደሚችል ይጠቁማሉ። 

ከትራንዚት ካርታ መመለስ በተጨማሪ በተጫዋቾች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ፣ እንደ ታንክ ፣ ታኪዮ እና ኒኮላይ ያሉ ቆየት ያሉ የዞምቢ ገፀ-ባህሪያትም ሊመለሱ እንደሚችሉ ተነግሯል። 

አሁኑ ላይ Black Ops 6 ዞምቢ ሞድ ላይ የተርሚነስ እና የላይቤሪቲ ፎልስ ካርታዎች ብቻ የሚገኙ ሲሆን ፥ ሁለቱም ካርታዎች ተጫዋቾች ሊፈቷቸው የሚችሏቸው ምስጢሮችን በውስጣቸው ይዘዋል። የምን ምስጢር ካላችሁ፦ 

የተርሚነስ ካርታን ምስጢር ለመፍታት Beamsmasher የተባለው የጦር መሳሪያ የሚያስፈልግ ሲሆን ፥ ላይቤሪቲ ፎልስ ላይ ደግሞ ጄት የተባለውን ሽጉጥ ተጫዋቾች በእጃቸው ሊያስገቡ ይገባል። 

ትራንዚትን መሠረት ተደርጎ የተሰራው ካርታ የሚወጣበት ቀን በግልጽ ባይታወቅም ፥ እነዚህ ፍንጮች እና በየቦታው ተበታትነው የሚገኙ እንቆቅልሾች ለዞምቢ ሞድ አድናቂዎች አስገራሚ ነገሮችን መክፈቻ ቁልፍ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል። 

 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !