
Pokémon TCG Pocket በየቀኑ ተሳትፎዎን ሊያጠናክሩ በሚችሉ አማራጮች የተሞላ ጌም ሲሆን ፥ ጊዜዎትን ሳያባክኑ ደረጃዎን ማሳደግ እንዲችሉ የሚያግዙ ፈጣን እና ቀላል የዕለት ተዕለት ሂደቶች እንደሚከተለው አዘጋጅተናል።
ጨዋታው በየቀኑ 7፡00 AM (የፈረንሳይ ሰዓት) ላይ የሚጀምር በመሆኑ ፣ በየቀኑ እነዚህን ሂደቶች ይከተሉ፦
ዕለታዊ ሽልማቶች፦ የመደብር ቲኬቶችን እና ሌሎች ሽልማቶችን በየዕለቱ ከጌሙ መደብር ይውሰዱ።
ዕለታዊ ተልዕኮዎችን ያጠናቅቁ፦ ሶስት ተልዕኮዎችን ሲወጡ 4 hourglass ቡስተሮችን ይሸለማሉ።
በየቀኑ 2 ነፃ ቡስተሮችን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ፣ ከፒካቹ ፣ ከቻሪዛርድ ወይም ከሜውትዎ ጥቅሎች መኃል የሚያስፈልግዎን ካርድ መርጠው መውሰድ ይችላሉ።
ተዕምረኛው መሳያ በሌሎች ተጫዋቾች የተገኙ ካርዶችን በዘፈቀደ እንዲስሉ ያስችልዎታል።
ተልዕኮዎችን ማጠናቀቅ እና ያልተለመዱ ካርዶችን ማግኘት እንዲችሉ ቢያንስ በቀን አንዴ ይጠቀሙበት።
ደረጃዎን ለመጨመር እና የተለያዩ ሽልማቶችን ለማስከፈት የብቃት ነጥቦችን ይሰብሰቡ።
ተጨማሪ ጉርሻዎችን ለማግኘት ተልዕኮዎችን ይወጡ።
ልምድ በማካበት ዴክዎን ያሻሽሉ።
ቢያንስ በቀን አንዴ ፣ ለብቻዎ ወይም ሌሎች ተጫዋች ጋር ውድድሮችን ቢያደርጉ ይመከራል።
የማህበራዊ ግንኙነት ገጽ ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር መገናኘት እንዲችሉ የተለያዩ አማራጮችን የሚሰጥ በመሆኑ ፣ እርስዎም፡-
የጓደኞችዎ ኤግዚቢሽኖች ላይ "Thumbs Up" በመስጠት ፣ ከመደብሩ ትኬቶችን እንዲሸለሙ ያድርጉ።
ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር መስተጋብሮችን እና ግንኙነቶችን ለመፍጠር ፣ የራስዎን ኤግዚቢሽን ያዘጋጁ።
ዝግጅቶች የተለያዩ ሽልማቶችን መሰብሰቢያ መንገዶች ስለሆኑ ፣ በመካሄድ ላይ የሚገኙ ዝግጅቶች ላይ ችላ ሳይሉ ይሳተፉ! ከጥቅሞቹም መካከል፦
ልዩ የፕሮሞ ካርዶች።
ልዩ ውድድሮች ላይ የመሳተፍ ዕድል።
ነፃ miracle hourglasses።
የጊዜ ገደብ ያላቸው ልዩ ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ እንዲችሉ በየሁለት ሰዓት ልዩነት ወደ ጌሙ ቢገቡ ይመከራል።
ከመደብሩ ያገኟቸውን ትኬቶች አስፈላጊ ሆኖ ካገኙት ፥ ወደ hourglasses ይለውጧቸው።
ወደ አንድ ምዕራፍ ማጠናቀቂያ መድረስ ከቻሉ ፥ 12 ተጨማሪ hourglasses መክፈት ስለሚችሉ ሂደትዎን ይከታተሉ።
እነዚህን የዕለት ተዕለት ተግባራት በየቀኑ በመተግበር ፣ በPokémon TCG Pocket ደረጃዎን ማሳደግ እና ጌሙ የሚያቀርባቸውን የተለያዩ ልዩ ልዩ ዕድሎች መጠቀም ይችላሉ።
መልካም ጨዋታ!