
በዲሴምበር 3፣ 2024 ላይ አዳዲስ ሰርቨሮች መጀመርን ተከትሎ፤ Dofus 3 ላይ በፍጥነት ደረጃዎን ለማሳደግ የሚረዳዎ ቀላል መመሪያ አዘጋጅተናል። የሚጫወቱት በአንድ አካውንት ይሁን በብዙ አካውንቶች፣ የአስራ ሁለቱ ዓለማትን መሰላል መንጠላጠል እንዲችሉ ቀጥለው የተቀመጡትን ሂደቶች ይከተሉ።
አጋዥ መመሪያ እና ኢንካርም
ልምዱ ካለዎት እና መሠረታዊ ነገሮችን ካወቁ፤ አጋዥ መመሪያውን በመዝለል በቀጥታ ወደ አስሩብ ይሂዱ።
ጅማሮ ተልዕኮዎች
የአስራ ሁለቱ መልዕክተኞችን ተልዕኮ ይቀበሉ እና አስሩብ ግንብ ላይ ተልዕኮውን ይወጡ።
በመቀጠል ተጨማሪ ተልዕኮዎችን ለመቀበል [5,-15] ላይ፣ ወደ Rogue Secret Passage ይሂዱ።
የአካሄድ ምርጫዎች
ሱፎኪያን ከመረጡ በአካባቢው ላይ የሚገኘው ፒዊስን ማደን ላይ ያተኩሩ።
እንደ አማራጭም፣ [-2፣13] ላይ ወደ ብራክማር በመሄድ ፒዊስን ማደን ይችላሉ።
ቀዳሚው ግብ
የመጀመሪያ መሳሪያዎን ማግኘት እንዲችሉ ፒዊስን ያሸንፉ እና አንዴ መሳሪያዎን ከታጠቁ በኋላ፣ ተልዕኮዎን ለማጠናቀቅ እና 20ኛው ደረጃ ላይ ለመድረስ ወደ ኢንካርናም በመመለስ Kardorim Dungeonን ያጠናቅቁ።
ተልዕኮውን ይጀምሩ፡-
ፊልድስ እስር ቤት መግቢያ ([7,-24]) አጠገብ የሚገኘውን ሜታግ ሮቢልን ያነጋግሩ እና የእስር ቤቱን ተልዕኮ ያጠናቅቁ።
አስትሮብ ታቨርን የሚገኘውን ተልዕኮ ከተወጡ በኋላ [1,-15] ላይ የምትገኘውን ኤማ ቶምፑስ ስለቀጣዩ ሂደት ያለነጋግሩ።
የእድገት ደረጃዎች፡-
የሞብ ስፖንጅ እና ሮያል ጎብቦል ተልዕኮን ያጠናቁ።
ደረጃ 40 ላይ ይድረሱ:
ደረጃዎ አነስተኛ ከሆነ Astrub እና Incarnam ውስጥ የሚገኙ የጭራቆች ስኬቶችን ያግኙ ወይም ተልዕኮዎችን ይወጡ።
ወደ ክዋክ ስብስብ ይቀይሩ፡-
+1 AP ጉርሻ የሚያሰጥ በመሆኑ ፒዊዎን በክዋክ ስብስብቦች ይተኩ።
እንዴት ማግኘት ይቻላል፦
እንደዞኖቻቸው ብዋክስ እና ክዋክስ ይሰብሰቡ።
የጭራቆች እጥረት ካጋጠመ ለክዋክ ደንጂን ቅድሚያ ይስጡ። ከፍተኛ ነጥቦችን የማግኘት እድልዎን ከፍ ለማድረግ ከጠላቶች አለቃ ጋር ከመዋጋትዎ በፊት ክፍሎቹን በፍጥነት ያጽዱ እና ይውጡ። በዛ ያሉ አባላት ያሏቸው ቡድኖች ብርቅዬ ሽልማቶችን የማግኘት ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው።
ከዚህ በመቀጠል በ "ክላሲክ" የደረጃ እድገት መንገድ ይቀጥሉ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛውን ደረጃ ላይ መድረስ ይችላሉ!