
ፎርትናይት አዲሱን Frenzy ወይም Ballistic ተብሎ የሚጠራውን ሞድ በማስጀመር የቪዲዮ ጌም ዓለሙን ሊቀይር ቆርጦ ተነስቷል። ይህ ሞድ ዲሴምበር 11፣ 2024 የተለቀቀ ሲሆን፣ ይህ ሞድ እንደ Counter-Strike እና Valorant ያሉ አንጋፋ ጌሞች ጋር የሚመሳሰል አስደሳች እና አስደናቂ ልምድንም ይሰጣል።
Frenzy ሞድ፤ ስልት፣ የቡድን ስራ እና ብቃት ቁልፍ የሆኑበት የ5v5 ግጥሚያ ሲሆን፤ ተጫዋቾች በሁለት ቡድን ይከፈሉ እና፣ የጥቃት ፈፃሚ ቡድኖች ግባቸውን በካርታው ላይ ከሚገኙት ሁለት ቦታዎች አንዱ ላይ rift trigger በማጥመድ ማፈንዳት ላይ ሲያደርጉ፤ ተከላካይ ቡድኖች ደግሞ ፍንዳታውን የማክሸፍ ተልዕኮን ይወጣሉ። እያንዳንዱ ግጥሚያ በርካታ ዙሮችን የሚያካትት ሲሆን 7 ዙሮችን በድል ያጠናቀቀ ቡድን አሸናፊ ይሆናል። በተጨማሪም በየ6 ዙሮች ሚናዎች የሚቀያየሩ በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ቡድን የማጥቃት እና የመከላከል እድል ማግኘት ያስችለዋል።
Frenzy ሞድን ልዩ ከሚያደርጉት ባህሪያት አንዱ ልዩ መሳሪያዎችን መጠቀም ማስቻሉ ሲሆን፤ ግጥሚያው ከመጀመሩ በፊት እያንዳንዱ ተጫዋች ከአምስት አማራጮች ውስጥ ማለትም ከproximity mine፣ protective bubble፣ recon grenade፣ frag grenade፣ እና repulsive grenade ውስጥ አንዱን የመምረጥ እድል ያገኛል። እነዚህ መሳሪያዎችም፣ የተጫዋቾችን ስልት በመጨመር አጨዋወታቸውን በመረጡት ዘይቤ እንዲያስተካክሉ ያስችሏቸዋል።
Frenzy ሞድ ሜጋሎፖሊስ 10 (ስካይላይን 10) ካርታ ላይ ብቻ የሚጀመር ሲሆን፣ አነስተኛ አቅም ያላቸው የጦር መሳሪያዎች እና ውስን ማሻሻያዎችንም ብቻ የሚያካትት ይሆናል። Epic Games ከተጫዋቾች የሚመጡ አስተያየቶችን መሰረት በማድረግ፤ በጊዜ ሂደት ተጨማሪ ይዘቶችን፣ አዳዲስ ካርታዎችን፣ መሳሪያዎችን እና አማራጮችን ለመጨመር አቅዷል።
Frenzy ሞድ ሁለት ዓይነት የግጥሚያ አማራቾችን የሚያቀርብ ሲሆን፡-
1. የደረጃ ሠንጠረዥ ያለው፦ አንድ ተጫዋች ድንገት ጨዋታውን ቢያቋርጥ መተካት የሚያስችል ሲሆን፣ ሚዛናዊነትን ለማረጋገጥም በቡድኖች አማካይ ደረጃ ላይ ተመስርቶ የሚዘጋጅ የግጥሚያ አማራጭ ነው።
2. ባለደረጃ ሠንጠረዥ፦ የደረጃ አሰጣጥ ስርዓትን የሚከተል እና ጨዋታውን በሚያቋርጡ ተጫዋቾች ላይ ቅጣትን የሚጥል አማራጭ ነው።
Epic Games በFrenzy ሞድ ታወቂ መካኒኮችን በማካተት እና ልዩ የሆነውን የፎርትናይት መለያ በመጨመር የነባር እና አዲስ ተጫዋቾችን ልብ በመግዛት፤ እንደ Counter-Strike እና Valorant ካሉ አንጋፋ የFPS ጌሞች ጋር ለመወዳደር ያሰበ ይመስላል።
Frenzy ሞድ Fortniteን የሚደግፉ ሁሉም የጌም መድረኮች ማለትም እንደ PlayStation 4 እና 5፣ Xbox One፣ Xbox Series X|S፣ PC፣ Nintendo Switch፣ Cloud Gaming እና ሞባይል ስልኮች ላይ ይገኛል።