
የፎርትናይት ተጫዋቾች የ2024 ጉዟቸውን መለስ ብለው መመልከት የሚችሉበት Fortnite Wrapped የተባለ አማራጭን በቅርቡ አስተዋውቋል። ይህ አማራጭ ከSpotify Wrapped ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ተጫዋቾች በዓመቱ ውስጥ ያገኟቸውን ስኬቶች እና ሂደቶች አስደሳች በሆነ ምስላዊ ይዘት እንዲያዩ ያስችላቸዋል።
የእርስዎን መግለጫ ለማግኘት፣ እነዚህን ቀላል ሂደቶች ይከተሉ፡-
ወደ Fortnite.GG ድረ-ገጽ ይሂዱ
Wrapped 2024 የሚለውን ገጽ ይክፈቱ
የEpic Games የተጠቃሚ ስምዎን፣ የXbox ጌመር ታግዎን ወይም የPSN መለያ ቁጥርዎን ያስገቡ።
ከአፍታ ቆይታ በኋላ፣ በዓመቱ ውስጥ የነበርዎትን ሙሉ ሂደቶች እና ስኬቶች ከሚስብ የይዘት አቀራረብ ጋር ይመጣልዎታል። ሪፖርቱ ውስጥ ከሚያገኟቸው ነገሮች መካከል፡-
ጠቅላላ የተጫወቷቸው ውድድሮች ብዛት
ድሎች (ቪክትሪ ሮያልስ)
ሽንፈት እና የጦር መሣሪያ አጠቃቀም መግለጫ
የሚወዷቸው ገፀ-ባህሪዎች፣ ልዩ እንቅስቃሴዎች (emotes) እና ማጌጫዎች
የውጊያ ማለፊያ ሂደቶችዎ በምዕራፍ ተከፋፍሎ
አጠቃላይ የጨዋታ ጊዜዎ
Fortnite Wrapped 2024 የእርስዎ የግል ስታቲስቲክስ ብቻ ሳይሆን፤ አጠቃላይ አፈጻጸምዎን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር እንዲያወዳድሩ ያስችልዎታል። እንደ ድሎች፣ ሽንፈቶች እና የጨዋታ ጊዜን መሠረት በማድረግ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ተጫዋቾች አንፃር ደረጃዎን ማየት ይችላሉ። እንዲሁም የእርስዎን ስታቲስቲክስ ከጓደኞችዎ ጋር ማወዳደር እና ማን ጥሩ ደረጃ እንዳለው እንዲያውቁ ያስችልዎታል።
አንዳንድ ተጫዋቾች በ2024 አስደናቂ አፈጻጸም ያስመዘግቡ ሲሆን፦
LM ABOOD 23,258 ድሎችን
Castella የተፎካካሪዎችን የማስወገድ ደረጃ ሠንጠረዙን በ305,909 በመምራት አንደኛ ላይ ይገኛል።
LRK ደግሞ ከ3,000 ሰዓታት በላይ ፎርትናይትን በመጫወት አሳልፏል።
እነዚህን ሂደቶች በመከተል የ2024 ስታቲስቲክስ ሪፖርትዎን፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በቀላሉ ማጋራት እና ለጓደኖችዎ መላክ ይችላሉ።