icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 1 ላይ የተካተቱ አዳዲስ ቦታዎች  

ዲሴምበር 1፣ 2024 ለጨዋታ የበቃው ፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 1 ፣ የጃፓኖችን ባህል መሠረት በማድረግ የተዘጋጁ አዳዲስ ካርታዎችን አካቷል። ይህ ልዩ ደሴት የተለያዩ መልክዓ ምድሮችን እና አዳዲስ ገጽታዎችን የሚያካተት በመሆኑ ጨዋታውን ልዩ ገጽታ ይሰጠዋል። 

ይህ አዲስ ካርታ ባህላዊ የጃፓን ገጽታን የተላበሱ አካባቢዎችን ከተለዋዋጭ መቼቶች ጋር የሚያጣምር ሲሆን ፤ ተጫዋቾች ሞቅ ደመቅ ያሉ ከተሞችን ፣ በበረዶ የተሸፈኑ ተራሮችን ፣ ፀጥታማ ስፍራዎች ላይ የሚገኙ ቤተ-መቅደሶችን እና ጥቅጥቅ ደኖችን እንዲያሰሱ ይስችላቸዋል። 

ዋና ዋና ቦታዎች (POIs 

  • Warrior's Watch፦ የጥንታዊ ጃፓናዊያን የሥነ-ህንፃ ጥበብ መሠረት በማድረግ የተሰራ ቤተ-መንግስት። 

  • Seaport City፡- የጃፓናዊያንን የወደብ ከተሞችን የሚያስታውስ ዘመናዊ ደማቅ ከተማ። 

  • Nightshift Forest፡- በድብቅ ምስጢሮች እና አስገራሚ ሁነቶች የተሞላ ፣ ምስጢራዊ ጫካ። 

  • Shining Span፡- ካርታው ላይ የሚገኙ ቁልፍ ቦታዎችን የሚያገናኝ ትልቅ ድልድይ። 

ተለዋዋጭ የጨዋታ መካኒክሶች 

  • ግዙፍ ተንቀሳቃሽ ዔሊ፡- ተጫዋቾች መደበቅ ወይም መንጠላጠል የሚችሉበት ተንቀሳቃሽ ዔሊ። 

  • ዘመናዊ ባቡር፡- ብዙ ህዝብ በሚበዛባቸው ከተማዎችን ውስጥ መጓጓዣ የሚያስችል ባቡር። 

  • ጋድዚላ፡- በፍልሚያ ወቅት የጥቃት አቅምን መጨመር የሚያስችል ጭራቅ። 

የጠላት አለቃዎች 

  • ጃይንት ሳሞራይ፡- ካርታው ላይ የሚገኙ ቁልፍ ቦታዎችን ጠባቂ። 

  • ፍላይንግ ኦኒ ማስክ፡- የሚያበሩ ቀያይ ዓይኖች ያሉት ፈታኝ አጋንንት። 

ተጨማሪ ቦታዎች 

  • ፈታኝ ውጊያዎችን ማስተናገጃ የፍልሚያ አውድማ። 

  • የግዙፉ ዔሊ መኖሪያ ሀይቅ። 

  • ባህላዊ የጃፓን ቤተ-መቅደስ እና ሌሎች የተደበቁ አካባቢዎች። 

ይህ ካርታ የጃፓን ባህልን፣ አፈ-ታሪካዊ ፍጥረታትን እና የተለያዩ ተጨማሪ መቼቶችን በማዋሃድ ፎርትናይት እስካሁን ከአዘጋጃቸው ካርታዎች ውስጥ እጅግ አስደናቂ ከሚባሉት ውስጥ መመደብ የሚችል ሲሆን፤ ይህ በምስጢሮች እና ፈታኝ ሁኔታዎች የተሞላ ደሴት ፥ የከተማ ሽምቅ ውጊያዎች፣ ተፈሯዊ አካባቢዎችን አሰሳ ወይም የጠላት አለቃዎች ጋር የሚደረጉ ፈታኝ ፍልሚያዎችን፣ በውስጡ የያዘ አስደናቂ ካርታ ነው። 

ለመጫወት ዝግጁ ነዎት? ዛሬውኑ የደሴቲቱን ምስጢሮች ማሰስ ይጀምሩ! መልካም ጨዋታ! 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !