
የፎርትናይት ምዕራፍ 6፣ ክፍል 1 የውጊያ ማለፊያ የተለያዩ ሽልማቶችን እና ገፀ-ባህሪዎችን በማካተት ዲሴምበር 1፣ 2024 በይፋ የተጀመረ ሲሆን፣ ይህ ምዕራፍ ተጫዋቾችን አጋንንቶች፣ አፈ-ታሪካዊ ፍጥረታት እና ሳሞራዎች የሚገኙበት የጃፓኖች ግዛትን የሚያስቃኝ ይሆናል።
የተካተቱ የውጊያ ማለፊያ ገፀ-ባህሪዎች
ኒያንጃ፦ የውጊያ ማለፊያ ሲገዙ ወዲያው ይከፈታል።
ጄድ፦ ልዩ የእስያ ዘይቤን የተላበሰ ገፀ-ባህሪ።
ኬንዶ፦ የጃፓናውያን ማርሻል አርትን መሠረት በማድረግ ተደርጎ የተሰራ ገፀ-ባህሪ።
ዳይጎ፦ የሳሙራይ ገጽታ ያለው ዋና ገፀ-ባህሪ።
ሆፕ ሻዶ ብሌድ፦ የታዋቂው ሆፕ ገፀ-ባህሪ ድጋሚ ስሪት።
ቤይማክስ ሂሮ፦ ተወዳጁ የዲስኒ ሮቦት።
ናይት ሮዝ፦ ጥቁር አልባሳትን የሚጠቀም አስፈሪ ገፀ-ባህሪ።
የተሻሻለው ጋድዚላ፦ ተጫዋቾች እስከ ጃንዋሪ 2025 ድረስ በመጠበቅ እና የውጊያ ማለፊያ ተልዕኮዎችን በማጠናቀቅ ይህን የውጊያ ማለፊያው ድምቀት የሆነውን የጋድዚላ ገፀ-ባህሪ ማስከፈት ይችላሉ።
አዳዲስ ማሻሻያዎች እና ሽርክናዎች
ይህ ምዕራፍ የጃፓናውያን ባህልን የሚያንፀባርቁ ቤተ-መቅደሶች፣ ሚስጥራዊ ፖርታሎች፣ አፈ-ታሪካዊ ፍጥረታት፣ ሳሙራይ፣ አዲስ ካርታ ላይ የሚገኝ ግዙፍ ድልድይን የሚያካተት ሲሆን በተጨማሪም፦
በውጊያ ማለፊያ በኩል ሊገኙ የሚችሉ ትናንሽ ሰው ለማድ ፍጥረታት።
በውጊያ ማለፊያ ውስጥ ያልተረጋገጠ ቢሆንም፣ የዲመን ስሌየር ሽርክና ሊኖር እንደሚችል ይገመታል።
በጋድዚላ እና ኪንግ ኮንግ መካከል የሚደረግ አስደናቂ ፍልሚያም የሚኖር ይሆናል።
የውጊያ ማለፊያ መግዣ ዋጋ
መደበኛ የውጊያ ማለፊያ ዋጋ፡- 1000 V-Bucks ሲሆን ቀድሞ ከነበረው ዋጋ በትንሹ ጨምሯል።
25 ተጨማሪ የሽልማት ጥቅሎች፦ 1800 V-Bucks
የውጊያ ማለፊያ + 25 የሽልማት ጥቅሎች ጥምር፦ 2800 V-Bucks።
ተጫዋቾች አሁንም የውጊያ ማለፊያ ደረጃቸውን በማሳደግ V-Bucksን ማግኘት ይችላሉ።
ተጫዋቾች የውጊያ ማለፊያ ለማጠናቀቅ እስከ ፌብሩዋሪ 21፣ 2025፣ 8 AM ድረስ ያላቸው ሲሆን፣ ሁሉንም ሽልማቶች ለማስክፈት እና ይህን ምዕራፍ ለማጣጣም በቂ ጊዜ ይኖራቸዋል።