
ፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 1 ዎል ባውንስ የሚባል አዲስ አሪፍ የእንቅስቃሴ ቴክኒክ አስተዋውቋል። ይህ ቴክኒክ ተጫዋቾች በፍጥነት ከግድግዳ ላይ ተወንጭፈው እንዲዘሉ የሚያስችላቸው በመሆኑ፣ ጌሙን ይበልጥ አስደሳች እና ሳቢ አድርጎታል።
እንዴት Wall Bounce ማድረግ ይቻላል፡-
በግራዎ ወይም በቀኝዎ በኩል ወደሚገኝ ግድግዳ በሩጫ ይዝለሉ
ግድግዳው ጋር እንደደረሱ የመዝለያ ቁልፉን ይጫኑ።
ይህም ወደ ግድግዳው ተቃራኒ በኩል ማለፍ እንዲችሉ፣ በፍጥነት እንዲንቀሳቀሱ ወይም ከዚህ ቀደም መድረስ የማይችሉባቸው ቦታዎችን እንዲደርሱ ያስችልዎታል።
ስለ Wall Bounce ጠቃሚ ምክሮች፡-
አቅምዎ ከማለቁ በፊት አራት ግድግዳዎች ድረስ መዝለል ይችላሉ።
ይበልጥ በነፃነት መንቀሳቀስ እንዲችሉ፣ የጠርዝ ዝላይ እና ሲያርፉ መንከባለልን እና የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ጋር በማዋሀድ ይጠቀሙበት። ይህ ዘዴ ጠላቶችችን ለማስደነቅ ወይም ከአደገኛ ሁኔታ በፍጥነት ለማምለጥ ሊያገለግልዎ ይችላል።
ዎል ቦውንስ በዚህ ምዕራፍ ከተዋወቁ የተለያዩ አዳዲስ የእንቅስቃሴ ቴክኒኮች አንዱ ሲሆን፣ ከዎል ባውንስ በተጨማሪም የጠርዝ ላይ ዝላይ፣ ተንከባሎ ማረፍ እና የግድግዳ ላይ ሩጫን ይገኙበታል። እነዚህ አዳዲስ እንቅስቃሴዎች ለተጫዋቾች ተጨማሪ ዘዴዎችን እና አዳዲስ ስልቶችን መጠቀም ያስችላቸዋል።
በWall Bounce እንደልብዎ እየተንቀሳቀሱ መዋጋት ይችላሉ። ከፈታኝ ውጊያዎች ለማምለጥ ወይም አስቸጋሪ ቦታዎች ላይ በፍጥነት ለመድረስ፣ እና አዳዲስ ስልቶችን መክፈት የሚያስችል ምቹ የእንቅስቃሴ ቴክኒክ ነው።
መልካም ጨዋታ! መልካም ዝላይ!