icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 1 ላይ እንዴት Ledge Jump ማድረግ ይቻላል? 

በፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 1 ላይ አዲስ ከተዋወቁት የእንቅስቃሴ ቴክኒኮች አንዱ የሆነው የጠርዝ ዝላይ ተጫዋቾች ከዚህ በፊት ካርታው ላይ ተደራሽ ያልነበሩ ቦታዎችን እንዲደርሱ የሚያስችል ልዩ ቴክኒክ ነው።  

Ledge Jumpን እንዴት መጠቀም ይቻላል፡- 

  • ወደ ጠርዝ ይሩጡ፡- ፊትዎን ወደ ህንፃ ጠርዝ ወይም ገደል ጫፍ በማድረግ ይሩጡ። 

  • ጠርዙ ላይ ሲደርሱ ይዝለሉ፦ የህንፃ ወይም የተራራ ጫፍ ላይ ሊደርሱ ሲሉ የዝላይ ቁልፉን ይጫኑ። ይህን ጊዜ ገፀ-ባህሪዎ ከወትሮው በተለየ ረጅም ርቀት ይዘላል። ይሁን እንጅ ቴክኒኩ እንዲሰራልዎ፣ ለመሮጥ የሚያስችል በቂ አቅም እንዳለዎት ቀድመው ያረጋግጡ። 

የጠርዝ ዝላይ ጥቅሞች፦ 

  • ከዚህ ቀደም ዘለው ሊደርሱባቸው የማይችሉ ቦታዎችን በአንድ ዝላይ ተወንጭፈው እንዲደርሱ ያስችልዎታል። 

  • ከቦታ ቦታ በነፃነት መንቀሳቀስ ያስችልዎታል 

  • ያልተጠበቁ ቦታዎች ላይ ድንገት በመከሰት ጠላቶችን ግራ ማጋባትም ይችላሉ። 

ከሌሎች ቴክኒኮች ጋር ማጣመር፦ 

  • ተንከባሎ ማረፍ፡- ወድቆ መጎዳትን ለማስቀረት፣ የጠርዝ ዝላይ ካደረጉ በኋላ ተንከባለው ይረፉ። 

  • የግድግዳ ዝላይ፦ ከፍታ ያላቸው ቦታዎች ላይ ለመድረስ የጠርዝ ዝላይ ካደረጉ በኋላ የግድግዳ ዝላይን ይጠቀሙ። 

  • የግድግዳ ላይ ሩጫ፦ ከተማዎችን በፍጥነት ለማሰስ የግድግዳ ላይ ሩጫ ቴክኒክ ጋር በማጣመር ይጠቀሙ። 

የጠርዝ ላይ ዝላይ ቴክኒክ ተጫዋቾች ፎርትናይት ላይ እንደልባቸው እየተንቀሳቀሱ የተለያዩ ከፍታዎች ላይ መዋጋት እንዲችሉ፣ ከዚህ ቀደም መድረስ የማይችሉባቸው አካባቢዎችን በቀላሉ ማሰስ እንዲችሉ፣ እንዲሁም ከጦርነት ለማምለጥ የሚያስችሉ አዳዲስ መንገዶችን ያቀርባል። 

መልካም ጨዋታ! መልካም ዝላይ! 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !