
ሊዮኔል ሜሲ ፎርትናይትን ተቀላቀለ! አዎ! ኢፒክ ጌምስ ታዋቂው አርጀንቲናዊን እግር ኳስ ተጫዋች ባትል ሮያልን መቀላቀሉን በይፋ አሳውቋል፣ ይህ በእግር ኳሱ ዓለም እና እጅግ ተወዳጅ በሆነው ቪዲዮ ጌም መካከል የተደረገው ታሪካዊ ሽርክናም በዓለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪ ርዕስ ሆኗል።
ስለዚህ ታሪካዊ ሽርክና ማወቅ ያለብዎት ጉዳዮች
የሚለቀቅበት ቀን፡- ዲሴምበር 14፣ 2024
መለዋወጫዎች እና መሸጫ ዋጋ
Streetwear Spark Messi፡- የሜሲ ገፅ-ባህሪ ከልዩ አልባስ ጋር በ1,500 V-Bucks።
ሊዮኔል ሜሲ፡- የሜሲ ገፅ-ባህሪ ከሁለት አማራጭ የእግር ኳስ አልባሳት ጋር በ1,500 V-Bucks።
የተሟላ ጥቅል፡- ሁለት መለዋወጫዎች፣ ሁለት ፒካክሶች፣ ሁለት ኢሞቶች እና የመሳሰሉትን በ2,800 V-Bucks (ወደ 22.99 ዩሮ አካባቢ)።
ምንም እንኳን ፎርትናይት ከዚህ በፊት እንደ ኔይማር ጁኒየር፣ ሄሪ ኬን እና ማርኮ ሬውስ ያሉ ኮከብ ተጫዋቾችን ያስተናገደ ቢሆንም ይህኛው ሽርክና ልዩ ተቀባይነትን አግኝቷል። ከታላላቅ የእግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ሜሲ መካተት ትልቅ ስኬትን የሚያመላክት እና በእግር ኳስ እና በቪዲዮ ጌሞዎች መካከል የሚደረጉ ቅንጅቶችን ጠቀሜታ አጉልቶ የሚያሳይ ጉዳይ ነው።
ተጫዋቾችም ይህን አስመልክቶ “ፎርትናይት ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል”፣ “ሜሲ ከዚህ በፊት ከነበሩ ገፀ-ባህሪዎች ጀግናው እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም”፣ “የመጀመሪያውን የፎርትናይት መለዋወጫዬን አሁኑኑ መግዛት አለብኝ” የሚሉ አስተያየቶችን በመስጠት የሚያስደንቅ ጉጉታቸውን ገልፀዋል። Streetwear Spark Messi የሚባለው አልባስም ጨዋታው የሚገኙ ድርጊቶችን መሰረት በማድረግ ገጽታን መለዋወጥ የሚያስችል አስደናቂ አልባስ ነው።
መድረኮች፡- PlayStation 5፣ PlayStation 4፣ Xbox Series X|S፣ Nintendo Switch እና PC ላይ ይገኛል።
ሊዮኔል ሜሲ በበኩሉ ትብብሩን አስመልክቶ “ፎርትናይትን ወክዬ ማየቴ ለእኔ እጅግ አስደናቂ ጉዳይ ነው፤ ይሄ ይሆናል ብዬ በፍጹም አስቤ አላውቅም ነበር።” በማለት የተሰማውን ደስታ ገልጿል።
ይህ በሜሲ እና ፎርትናይት መካከል የተደረገው ትብብር አዲስ ማጌጫዎችን ከማካተት በላይ የሆነ፣ ለሁለቱም የእግር ኳስ እና የቪዲዮ ጌም አድናቂዎች ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ተሞክሮን የሚሰጥ ታላቅ አጋጣሚ ነው። ፎርትናይት የማይደፈሩ ድንበሮችን በመግፋት ፣ እያንዳንዱን ትብብር ዓለም አቀፋዊ ክስተት ማድረጉን ቀጥሏል።