
የMarvel Rivals አድናቂዎች፣ እንኳን! እንኳን! ደስ ያላችሁ! መነሻውን ከማርቭል ዩኒቨርስ ያደረገው ኃያሉ እና አስፈሪው አልትሮን የNetEase ጌሞች ዝርዝርን ሊቀላቀል ሲሆን፣ የአይረን ማን ፈጠራዎችን መሠረት በማድረግ የተዘጋጀው አልትሮን የድጋፍ እና የማጥቃት ብቃቶቹን በማጣመር ጨዋታውን ለመቀየር ተዘጋጅቷል።
ምንም እንኳን የሚለቀቅበት ቀን በይፋ የተገለጸ ባይሆንም፣ አፈትልከው የወጡ በርካታ ፍንጮች፣ አልትሮን ምዕራፍ 1 ሲጀመር የሚኖሩት የመጀመሪያ ሳምንታት ውስጥ ሊለቀቅ እንደሚችል ይጠቁማሉ። ስለዚህ ከአሁኑ ይዘጋጁ!
የአልትሮን ልዩ ችሎታዎች
አልትሮን ከፍተኛ ጥቃቶችን በማድረስ እና ለአጋሮቹ አስተማማኝ ጋሻ በመሆን የሚታወቅ ሲሆን፣ ልዩ ችሎታዎቹም፦
ኢንሴፋሎ-ሬይ፡- ጠላቶችን ድምጥማጣቸውን ማጥፋት የሚችል የጨረር ጥቃት።
አልጎሪዝም ኮሬክሽን፡- የመዝለያ ቁልፍን በመያዝ ልዩ የማንዣበብ ብቃት።
ዳይናሚክ ፍላይት፡- በመረጡት አቅጣጫ ተወንጫፊ በረራዎችን ማድረግ።
ኢምፓራቲቭ ፋየርዎል፡- በአቅራቢያዎ የሚገኙ አጋሮችዎን ህይወት ማደስ የሚችሉ ትናንሽ ድሮኖችን ይጠራል።
ኢምፓራቲቭ ፓች፡- የመረጡትን አጋር ህይዎት መፈወስ እና የቡድን አጋሮችዎን መርዳት የሚያስችል ትልልቅ ድሮኖችን ያሰማራል።
ሬጅ ኦፍ አልትሮን (ከፍተኛ)፡- እንደየሁኔታው ጠላቶችን በጨረር ማጥቃት ወይም አጋሮችን መፈወስ የሚያስችሉ በርካታ ድሮኖች ይለቃል።
ዲሴምበር 6፣ 2024፣ Xbox Series X|S፣ PS5 እና PC ላይ ከተለቀቀ በኋላ Marvel Rivals በርካታ የሚባሉ ተጫዋቾችን መሳብ የቻለ ሲሆን፣ የአልትሮን መካተት NetEase ጌሙን ይበልጥ አጓጊ እና አሳታፊ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
የአልትሮን ገፀ-ባህሪን ተላብሰው ለመጫወት ጉጉት ላይ ከሆኑ ይፋዊ ማሳወቂያዎችን መከታተልዎን አይዘንጉ።
አልትሮን መጪ ፍልሚያዎች ላይ ቁልፍ ስልታዊ አማራጭ ለመሆን መዘጋጀቱ ምንም የማያጠራጥር ጉዳይ ነው!