icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ፉትቦል ማናጀር በ2025 እንደማይለቀቅ ስፖርትስ ኢንተራክቲቭ አሳወቀ  

ለፉትቦል ማናጀር አድናቂዎች ሰበር ዜና! ስፖርትስ ኢንተራክቲቭ ፉትቦል ማናጀር በ2025 እንደማይለቀቅ እና ለ2026 መዟዟሩን በይፋ ገልጹ። 

ለምን ከ2025 ወደ 2026 ተዘዋወረ? 

በመጀመሪያ ኖቬምበር 2024 ይለቃቃል ተብሎ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም፣ ድጋሚ ወደ ማርች 2025 እንዲዘዋወር ተደርጎ ነበር። FM 2025 በዩኒቲ የተዘጋጀ የግራፊክስ ሞተር እና የሴቶች እግር ኳስን ያስተዋውቃል ተብሎ የሚጠበቅ ጌም የነበረ ሲሆን፣ ሆኖም ግን፣ ጌሙ በሚዘጋጅበት ወቅት ቴክኒካል እክሎች ዝግጅቱን ከባድ እንዳደረጉት እና ሙሉ በሙሉ ሳይዘጋጅ ቢለቀቅ የፍራንቻይዙን ጥሩ ስም ሊያበላሽ እንደሚችል ስፖርትስ ኢንተራክቲቮች ገልጸዋል። 

ይህን ተከትሎም አንዳንድ ተጫዋቾች ስፖርትስ ኢንተራክቲቭ ለጥራት የሚሰጠውን ትኩረት ሲያደንቁ፣ ሌሎች ደግሞ ዘግይተው ማሳወቃቸውን እና ቃላቸውን መጠበቅ አለመቻላቸውን ተችተዋል። 

FM 2025ን ቀድመው አዘው የነበሩ ተጫዋቾች ገንዘባቸው ሙሉ በሙሉ ተመላሽ ይደረግላቸዋል። 

ስፖርትስ ኢንተራክቲቮች FM 2026 በግራፊክስ፣ በጨዋታ እና በቴክኖሎጂ ትልቅ ማሻሻያዎችን ያካተተ ታሪካዊ ጌም እንደሚሆን ቃል ገብተዋል። 

ተጫዋቾች ፉትቦል ማናጀርን ረዘም ላለ ጊዜ መጠበቅ የሚኖርባቸው ቢሆንም፣ ስፖርትስ ኢንተራክቲቭ ተጫዋቾችን ለመካስ በቁርጠኝነት የተነሱ ይመስላሉ። 

 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !