icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

እውነት GTA 6 እ.ኤ.አ በ2025 ይለቀቃል ወይስ አይለቀቅም? 

ከአስር ዓመታት በላይ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እና በሮክስታር ጌሞች የሚዘጋጀው Grand Theft Auto VI እ.ኤ.አ በ2025 እንደሚለቀቅ ተነግሯል። የሮክስታር ጌምስ እህት ኩባንያ የሆነውም ቴክ-ቱ ኢንተራክቲቭ የፋይናንሺያል ስኬቶቹን በሚያቀርብበት ወቅት የመለቀቁን ጉዳይ አረጋግጠዋል፣ ይህም ሊዘገይ የሚችልበት ምንም ምክንያት እንደሌለ ማረጋገጫ ነው። 

ለቴክ-ቱ ኢንተራክቲቭ ወሳኝ ዓመት 

የቴክ-ቱ ኢንተራክቲቭ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ስትራውስ ዘልኒክ እ.ኤ.አ. 2025 ለአሳታሚው ሪከርድ መሰባበሪያ ዓመት እንደሚሆን የገለጹ ሲሆን፣ ከጂ.ቲ.ኤ 6 በተጨማሪም ሲቪላይዜሽን VII፣ ማፊያ፡ ዘ ኦልድ ካንትሪ እና ቦርደርላንድስ 4ን እና የመሳሰሉ ሌሎች አንጋፋ ጌሞች ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። 

ምን አዲስ ነገሮች ይኖራሉ? 

እ.ኤ.አ ዲሴምበር 2023 የተለቀቀው የGTA 6 የመጀመሪያው ማስታወቂያ ላይ የሚከተሉት ታይተዋል፡- 

  • በዘመናዊ መልኩ የማያሚ ከተማን መሠረት በማድረግ ድጋሚ የተሰራ የቫይስ ሲቲ መመለስ። 

  • አስደናቂ ጀብዱዎች፣ ቅንጡ ፓርቲዎች፣ ሰፊ እና ዘርፈ ብዙ የሆነ ካርታ። 

  • በፍራንቻይዙ ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት ገጸ-ባሕሪ የሆነችው ሉቺያ። 

ምንም እንኳን እነዚህ ፍንጮች ቢኖሩም ሮክስታር እስካሁን በይፋ የገለጸው ነገር የለም። ከመጀመሪያው ማስታወቂያ ቪዲዮ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ምንም ተጨማሪ መረጃዎች ያልተገለጹ ሲሆን፣ አንዳንዶች ማስታወቂያው በዋናነት ባለድርሻ አካላትን ለማረጋጋት ተብሎ እንደተለቀቀ ሃሳባቸውን ገልፀዋል። 

GTA V ወደ 200 ሚሊዮን የሚጠጉ ቅጂዎችን መሸጥ የቻለ ጌም ሲሆን፣ ይህም ስኬት GTA 6 እጅግ ከፍተኛ ተጠባቂ እንዲሆን ስለሚያደርገው ሮክስታር ከሚጠበቀው በላይ በሆነ መልኩ GTA 6ን የማቅረብ ትልቅ ኃላፊነት ይጥልበታል። 

አታሚው ቴክ-ቱ GTA 6 እንደታቀደው በ2025 እንደሚለቀቅ በሙሉ መተማመን የተናገረ ቢሆንም፣ አዳዲስ መረጃዎች ወጥተው ቀኑን እስከሚያረጋግጡ ድረስ፣ አጠራጣሪነቱ እንዳለ ይቆያል። 

ሮክታር በጊዜ መርሐ ግብሩ ይጸናል ወይንስ GTA 6 ድጋሚ ይራዘማል? መልሱ በሚቀጥሉት ወራት የምናይ ይሆናል። 

 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !