
ፎርትናት ምዕራፍ 6 ክፍል 2፣ «ሎውለስ» በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ ፌብሪዋሪ 21፣ 2025 ላይ ከአዲሱ 34.00 ዝመና ጋር ተለቋል። ይህ ዝመና ጌሙን አዲስ ገጽታ እና አሳታፊ የሚያደርጉ የተሻሻሉ ቦታዎችን፣ ልዩ ገፀ-ባህሪዎችን፣ አዳዲስ የጦር መሳሪያዎችን፣ እና ሌሎች በርካታ የጨዋታ ማሻሻያዎችን ያካተታል።
ክራይም ሲቲ፡- በወንጀል የተሞላ ከተማ።
አውትሎው ኦሲስ፡- ሕግ አልባ በረሃ ላይ የሚገኝ መደበቂያ።
ሻይኒ ሻፍትስ፡- የሚያበሩ እና በምስጢር የተሞሉ ዋሻዎች።
ሎንዎልፍ ላየር፡- ምስጢራዊ ምሽግ።
የሚዳስ ፐምፕ ጠመንጃ፡- ወርቃማው ንጉስን መሰረት በማድረግ የተሰራ ከፍተኛ ኃይል ያለው ጠመንጃ።
አኪምቦ SMGs፡- የተኩስ ኃይልን በእጥፍ መጨመር የሚያስችል ባለሁለት አፈሙዝ አውቶማቲክ ጠመንጃ።
የሞርታል ኮምባት ልዩ የጦር መሳሪያዎች፡- የሰብ-ዜሮ ማድረቂያ መሳሪያ።
የኤሌክትሪክ የቤዝቦል ዱላ፡- ከያኩዛ የትብብር ሽርክና ጋር የተያያዘ መሳሪያ።
ቮልቸርስ አይ፦ ያስወገዷቸውን ጠላቶች ካርታው ላይ ያሳያል።
ጎልደን ረሽ፦ ሣጥኖችን ሲሰብሩ ወይም ሲከፍቱ የወርቅ ክምሮችን ያስገኛል።
አድሬናሊን ሰርጅ፦ ግድግዳ ላይ ሲወጡ፣ ሲንጠላጠሉ ወይም ሲነጥሩ ጥንካሬን ይመልሳል።
ጎልደን ኤሞ፦ ወርቆችን በሚሰበስቡበት ወቅት ተጨማሪ የሽጉጥ ቀልሃዎችን ይሰጣል።
ግሪድ፦ ጠላቶችን ከማስወገድ እና ከሣጥኖች የሚገኙ የወርቅ ገቢዎችን ይጨምራል።
የተሻሻለ የባቡር ሲስተም፡- የባቡር ሲስተሙ የተሻሻለ ሲሆን፣ አሁን ላይ ውጊያዎች ላይ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
የተሻሻሉ ቱሬቶች፡- ቱሬቶች ከአዲስ የማስተካካያ አማራጮች ጋር ተመልሰዋል።
የውጊያ አነስተኛ አውቶብስ፡- ደሴቲቱ ላይ ያለ ምንም የደህንነት ስጋት ሊጓጓዙበት የሚችሉበት መኪና።
አዲስ ሜዳሊያዎች፡- ተጨማሪ ኃይል የሚሰጡ እና እንዲያሸንፉ የሚረዱ ልዩ ግብዓቶች።
ተጫዋቾች XPዎችን ለማግኘት እና የባትል ፓስ ደረጃቸውን ለማሳደግ በየሳምንቱ ማክሰኞ ተልዕኮዎችን ማጠናቀቅ ይችላሉ። እንዲሁም ምስጢራዊ ተልዕኮዎች እና ልዩ ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ ተጨማሪ XPዎችን ማግኘት ይችላሉ።
የፎርትናይት 34.00 patch አዳዲስ መካኒክሶችን፣ በጀብድ የተሞሉ ውጊያዎችን እና ቢያሰሷቸው የማያልቁ አዳዲስ ቦታዎችን ለተጨዋቾች ያቀርባል።