
እ.ኤ.አ በፌብሩዋሪ 21፣ 2025 የወንጀል እና የዝርፊያ ጭብጥ ያለው ፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 2 «ሎውለስ» ለጨዋታ የበቃ ሲሆን፣ ይህ ምዕራፍ ለተጫዋቾች ልዩ ሽልማቶችን፣ ልዩ ገፀ-ባህሪዎችን፣ መለዋወጫዎችን፣ ተልዕኮዎችን እና በአዳዲስ ይዘቶች የተሞላ ባትል ፓስ ይዞ መጥቷል።
አዲስ የተካተቱ ገፀ-ባህሪዎች፡-
አውትሎው ሚዳስ፡- ራሱ ሚዳስ ሆኖም ግን የወንጀለኛ ገፀ-ባህሪን የተላበሰ።
ካሲዲ ክዊን፡- ባትል ፓሱን እንደገዙ ወዲያው ማግኘት ይችላሉ።
ጆስ፡- የኬሚስትሪ ይዘት ያለው ኦሪጅናል ገጸ-ባህሪ።
ፍሌቸር ኬን፡- በጎም ክፉም ጎን ያለው ሲሆን፣ ነጣ እና ጠቆር ባሉ ስታይሎች ሊገኝ ይችላል።
ቫለንቲና፡- ተንኮለኛ እና የተዋጣላት ዘራፊ።
ቪቶ ኮርኒቾን፡- ዘዴኛ እና ራፕ የሚያደርግ ፒክል።
ኬሻ ክሮስ፡- በተለያዩ መንገዶች መዋጋት የምትችል ጠንካራ ተዋጊ።
ሰብ-ዜሮ (MK3) እና ስኮርፒዮን፡- የሞርታል ኮምባት ታዋቂ ገጸ-ባህሪያት ሲሆኑ፣ የጌሙ መደብር ሊያገኟቸው ይችላሉ።
የባትል ፓስ መሸጫ ዋጋ 1,000 ቪ-በክስ ሲሆን፣ ለሁሉም ተጫዋቾች አንዳንድ ነፃ ሽልማቶችም ይኖራሉ፦
ሃት ፖከር (መጥረቢያ)
ፒርሲንግ ኤስ (መርጫ)
ዲለርስ ዴክ (መንሳፈፊያ)
100 ቪ-በክስ
ጎልደን ዎልፍ (መርጫ)
ሎን ዎልፍ ሆልስተር (ቦርሳ)
ጂጂ ከድልስ (የመሳሪያ ማስጌጫ)
ከድልስ ጋርደን (መርጫ)
ፕሪሚየም ሽልማቶች፦
ፕሪሚየም ሽልማቶች እንደ አውትሎው ሚዳስ፣ ፍሌቸር ኬን እና ኬሻ ክሮስ ያሉ ልዩ ገፀ-ባህሪዎችን፣ የተለያዩ መለዋወጫዎች እና ማስጌጫዎችን ያካትታል።
ተጫዋቾች XPዎችን ለማግኘት እና የባትል ፓስ ደረጃቸውን ለማሳደግ በየሳምንቱ ማክሰኞ ተልዕኮዎችን ማጠናቀቅ ይችላሉ። እንዲሁም ምስጢራዊ ተልዕኮዎች እና ልዩ ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ ተጨማሪ XPዎችን ማግኘት ይችላሉ።
በጥቁር ገበያዎች ወይም ብርቅዬ ሣጥኖች ውስጥ የሚገኝ አዲስ ብለስ የተባለ የጥቅማጥቅሞች ሲስተም፡-
ቮልቸርስ ብለሲንግ፦ ያስወገዷቸውን ጠላቶች ካርታው ላይ ያሳያል።
ጎልደን ረሽ ብለሲንግ፦ ሣጥኖችን ሲሰብሩ ወይም ሲከፍቱ የወርቅ ክምሮችን ያስገኛል።
አድሬናሊን ሰርጅ ብለሲንግ፦ ግድግዳ ላይ ሲወጡ፣ ሲንጠላጠሉ ወይም ሲነጥሩ ጥንካሬን ይመልሳል።
ጎልደን ኤሞ ብለሲንግ፦ ወርቆችን በሚሰበስቡበት ወቅት ተጨማሪ የሽጉጥ ቀልሃዎችን ይሰጣል።
ግሪድ ብለሲንግ፦ ጠላቶችን ከማስወገድ እና ከሣጥኖች የሚገኙ የወርቅ ገቢዎችን ይጨምራል።
አዲሱ ፎርትናይት ምዕራፍ 6 ክፍል 2 ሁሉም መድረኮች ላይ የሚገኙ ተጫዋቾችን የሚያስደስቱ አዳዲስ ገፀ-ባህሪዎችን፣ ሽልማቶችን እና መካኒክሶችን ከላይ በዝርዝር ባስቀመጥናቸው መልኩ ያቀርባል።