icon-menu.svg

Estás suscrito a Chefbook

Barra libre de artículos de viajes

SUSCRÍBETE a Chefbook por 2,99€/semana

IVA incluido y no te pierdas nada.

ሞነስተር ሃንተር ዋይልድስላይ እንዴት ዳፐርዊንግን መያዝ ይቻላል? 

ሞነስተር ሃንተር ዋይልድስ ላይ ተጫዋቾች ግዙፍ ፍጥረታትን ከማደን በተጨማሪ ብርቅዬ ከሆኑ ትናንሽ እንስሳት ጋር መስተጋብር መፍጠር ይችላሉ። ከእነዚህም ፍጥረታት መካከል የተመራማሪዎችን እና የአዳኞችን ትኩረት መሳብ የቻለችው ባለአረንጓዴ ላባዋ ወፍ ዳፐርዊንግ ነች። ይችን ወፍ መያዝ ተጨማሪ ተልዕኮ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ጌሙ ሥነ-ምህዳር ጠልቆ መግባትም ያስችላል። 

የተልዕኮው አጠቃላይ እይታ 

ብዙውን ጊዜ ዳፐርዊንጎችን የሚያገኟቸው ማርኮዳ ሊዛርድን የሚመለከት ተልዕኮ ላይ ዳሪልን ከረዱ በኋላ ሲሆን፥ ይህን ተከትሎም የዱር አራዊት ተመራማሪ የሆነው ሳሚን ለጥናቱ ዳፐርዊንግ እንዲይዙለት እርዳታዎን ይጠይቃል። ይህም ተልዕኮም ወደ ስካርሌት ጥቅጥቅ ደን እና ምስጢራዊ ቦታ ይወስድዎታል። 

በደማቅ አረንጓዴ ላባዎቿ የምትታወቀው ዳፐርዊንግ እንደ ቅርንጫፎች፣ ቋጥኞች እና ፍርስራሽ መዋቅሮች ባሉ ከፍተኛ ቦታዎች ላይ በአብዛኛው ትገኛለች። አንዳንድ ዳፐርዊንጎች ሥጋ በል የሆኑ እፅዋት ላይ ሲያርፉ ይታያሉ። ሆኖም ግን እነዚህ የታሪኩ አካል የሆኑ ትዕይንቶች በመሆናቸው ሊያዙ አይችሉም። 

ዳፐርዊንጎችን የማግኘት እድልዎን ለመጨመር፦ 

  • የተሻለ ማየት እንዲችሉ ስካርሌት ጫካን ከማታ ይልቅ ቀን ላይ ያሰሱ። 

  • በተለይ ዞን 14 ውስጥ ለዳፐርዊንጎች አመች ማረፊያ ቦታዎች ስለሚገኙ፣ ትኩረት ይስጡት። 

እንዴት እነዚህን ወፎች ማጥመድ ይቻላል? 

  • የመሳሪያ ስብስብዎ ውስጥ የሚገኘውን የማጥመጃ መረብዎን ይታጠቁ። 

  • ድንገተኛ እንቅስቃሴዎች እነዚህን ወፎች ስለሚያስበረግጋቸው ዓላማዎን ሳያሳኩ እንዳይበሩ በጥንቃቄ ይቅረቡ። 

  • ወፎቹ በርግገው እንዳይበሩ እና ሳይታዩ መቅረብ እንዲችሉ የጊሊ ማንትል መሰውርን ይጠቀሙ። 

  • ድምጽዎን አጥፍተው አንዴ ከተጠጓቸው በኋላ የማጥመጃ መረብዎን በማነጣጠር ወደ ዳፐርዊንጎቹ ያስወንጭፉ። 

ሽልማቶች 

ይችን ብርቅዬ ወፍ ከያዙ በኋላ ሳሚን ወደሚገኝበት ዋና ካምፕ ይመለሱ። እንደ እንጉዳይ እና ማር ያሉ ሽልማቶችን ከተጨማሪ የጊልድ ነጥቦች ጋር ይሸለማሉ። ሽልማቱ መጠነኛ የሚባል ቢሆንም፣ ጨዋታው ውስጥ ደረጃዎን ለማሳደግ እና ብርቅ ሀብቶችን ለማስከፈት ያገለግሉዎታል። 

icon-x.svg

icon-x.svg

You are in offline mode !